በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ይመጣል—ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያየው የተስፋ ራዕይ


ራዕይ

ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ይመጣል

ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያየው የተስፋ ራዕይ

ዮሐንስ ከኢየሱስ ክርስቶስ አጠገብ ቆሞ።

ሐዋርያው ዮሐንስ ልዩ ራዕይ አይቶ ነበር። ዮሐንስ ስላለፈው እና ስለወደፊቱ ብዙ ነገሮችን ያሳየውን ኢየሱስ ክርስቶስን አየ። እርሱም ዮሐንስ ያየውን እንዲጽፍ ነገረው። ኢየሱስ ቅዱሳን እርሱን ለመከተል የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ እንደሆነ ያውቅ ነበር። ኢየሱስ በአለም ካለው ክፉ ነገር ይልቅ እርሱ ሃያል እንደሆነ ተስፋ እንዲያደርጉ ፈልጎ ነበር።

ራዕይ 1፥1–2፣ 9–11፣ 13–15፣ 192–3

የሰማይ አባት በኢየሱስ ትከሻ ላይ እጁን አድርጎ።

ዮሐንስ በራዕዩ ማንም ሊከፍተው የማይችለውን መጽሐፍ አየ። ከዚያም መጽሐፉን ሊከፍት የሚችለውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚወክለውን በግ ዮሐንስ አየ። ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የሰማይ አባት ኢየሱስ አዳኛችን እንዲሆን መረጠው። ይህ ኢየሱስ ብቻ ሊያደርገው የሚችለው እጅግ አስፈላጊ የሰማይ አባት እቅዱ ክፍል ነበር።

ራዕይ 5

ሰይጣን እና የመንፈስ ልጆች ስብስብ ሰማይን ለቀው ሲሄዱ።

ዮሐንስ ሰይጣንን የሚወክለውን ዘንዶ አየ። ሰይጣን የእግዚአብሔርን ዕቅድ አልወደደም። በሰማይም ጦርነትን ቀሰቀሰ። አብዛኞቹ የሰማይ አባት የመንፈስ ልጆች በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ነበራቸው እንዲሁም እርሱን ለመከተል መረጡ። ነገር ግን ጥቂቶቹ ሰይጣንን ለመከተል መረጡ። በምርጫቸውም ምክንያት ከሰማይ ተባረሩ።

ራዕይ 12፥3–11

በአንድነት የሚሄዱ ወታደሮች፣ የተቸገሩ ሰዎችን፣ እና ረሃብን የሚያሳይ ጥምር ፎቶ።

ሰይጣን እና የእርሱ ተከታዮች ኢየሱስን እና በምድር ያሉ የእርሱ ተከታዮችን ማጥቃት እንደቀጠለ ዮሐንስ ተመለከተ። ሰዎች የኢየሱስን ወንጌል እንዳያምኑ ሊያታልሏቸው ሞከሩ። ብዙ ጦርነት፣ ጥፋት፣ እና በሽታ ነበር።

ራዕይ 68–912፥1713፥11–1817–18

መልአኩ ሞሮኒ ጆሴፍ ስሚዝን ወደ ወርቁ ሰሌዳዎች እየመራው።

ነገር ግን የሰማይ አባት በምድር ላሉ ሁሉ ይዳረስ ዘንድ መላዕክትን ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ጋር ከሰማይ ላካቸው።

ራዕይ 14፥6–7

ቤተሰብ ቅዱስ ቁርባንን እየተካፈሉ።

አንዳንድ ሰዎች በሰማይ እንዳደረጉት በኢየሱስ ያምናሉ እንዲሁም የእርሱን ትዕዛዛት ይጠብቃሉ። በኢየሱስ ያላቸው ምስክርነት ከሰይጣን ጋር በሚደረገው ጦርነት ይረዳቸዋል።

ራዕይ 12፥1119፥8–10

መላዕክት ከበስተኋላው ሆነው ኢየሱስ ከሰማይ እየወረደ።

ዮሐንስ ኢየሱስ ዳግም ወደ ምድር እንደሚመጣ አየ። እርሱ የዓለም ሁሉ ንጉሥ ይሆናል። ሰይጣን ከዚህ በኋላ ምንም ሃይል አይኖረውም። በኢየሱስ ምክንያት፣ ምንም ዓይነት ሃዘንም ሆነ ህመም አይኖርም። በኢየሱስ የሚያምኑ እንዲሁም ከእርሱ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳኖች የሚጠብቁ ሁሉ ከእርሱ እና ከሰማይ አባት ጋር ለዘለአለም ይኖራሉ።

ራዕይ 19፥–11–1620፥1–221፥1–7