በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ማርታ እና ማርያም—በጣም አስፈላጊ የሆነውን መምረጥ


ሉቃስ 10፥38–42

ማርታ እና ማርያም

በጣም አስፈላጊ የሆነውን መምረጥ

ማርታ ኢየሱስን እና ደቀመዛሙርቱን ስትቀበል።

ማርታ ቢታንያ በተባለ መንደር ትኖር ነበር። ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ ወደ ቢታንያ ሲመጡ ማርታ ወደ ቤቷ ተቀብላ ታስተናግዳቸው ነበር።

ሉቃስ 10፥38

ማርታ እንግዶቿን ስታስተናግድ።

ኢየሱስ ሲያስተምር፣ ማርታ እንግዶቿን በማስተናገድ በጣም ተጠምዳ ነበር። እህቷ ማርያም ከኢየሱስ አጠገብ በመሆን የሚናገረውን ትሰማ ነበር።

ሉቃስ 10፥39-40

ማርታ ኢየሱስን ስታናግር።

ማርታ ብቻዋን ስራውን ሁሉ እየሰራች በመሆኑ ደስተኛ አልነበረችም። ማርያም ኢየሱስን ከመስማት ይልቅ እርስዋን መርዳት እንዳለባት አስባለች። ማርታ ማርያም እርሷን እንድትረዳ እንዲነግራት ኢየሱስን ጠየቀችው።

ሉቃስ 10፥40

ኢየሱስ ለማርታ ሲመልስላት።

ኢየሱስ ማርታ እንዴት ጠንክራ እየሰራች እንደነበር ማየት ችሏል። እርሱም በብዙ ነገር እየታወከች መሆኗን እንደተገነዘበ ነግሯታል።

ሉቃስ 10፥41

ኢየሱስ ማርታን እና ማርያምን እያስተማረ።

አንዳንድ ነገሮች ከሌሎች ነገሮች ይበልጥ አስፈላጊ እንደሚሆኑ አብራራላት። ማርያም፣ እርሱም አለ፣ የእርሱን ቃላት ለመስማት ባደረገችው ምርጫ መልካም አድርጋለች። ከኢየሱስ እየተማረች የነበሩት ነገሮች ከእርስዋ በጭራሽ አይወሰዱባትም።

ሉቃስ 10፥42