ሉቃስ 7፥36–50
ኢየሱስ አንዲትን ሴት ይቅር አላት
“እጅግ ወዳለች”
ስምኦን የተባለ ሰው ኢየሱስን ወደ ቤቱ እንዲመጣ እና አብረው እንዲበሉ ጋበዘው። ስምኦን ፈሪሳውያን ከሚባሉ መሪዎች መካከል አንዱ ነበር።
ሉቃስ 7፥36
እየበሉም ሳለ፣ ሴቲቱ ወደ ስምኦን ቤት መጣች። ኢየሱስም በዚያ እንደነበር ሰምታ ነበር። ለእርሱ ያላትን ምስጋና እና ፍቅር ለማሳየት ፈለገች።
ሉቃስ 7፥37
እርስዋም ኢየሱስን ባየች ጊዜ አለቀሰች። እንባዎቿም እግሮቹን አጠቡ። ከዚያም እግሮቹን በጸጉሯ አደረቀች። እግሮቹንም ሳመቻቸው በሽቶም ዘይት ቀባቻቸው።
ሉቃስ 7፥38
ይህች ሴት ብዙ ሃጢያቶችን እንዳደረገች ስምኦን ያውቅ ነበር። እርሱም፣ በእውነት ኢየሱስ የእግዚአብሔር ሰው ቢሆን ኖሮ ይህች ሴት ሃጢያተኛ መሆኗን ያውቅ ነበር እና እንድትነካውም አይፈቅድላትም ነበር በማለት አሰበ።
ሉቃስ 7፥39
ኢየሱስም ስምኦን ምን እያሰበ እንደነበር ያውቅ ነበር። ሴቲቱ እግሩን ያጠበችው ስለምትወደው እንደነበር ለስምኦን ነገረው። በተለምዶ እንግዶች የራሳቸውን እግር እንዲያጥቡ ውሃ ይሰጣቸዋል። ስምኦን ለኢየሱስ ፍቅርን ለማሳየት እንዲህ ያለ ነገር በጭራሽ አላደረገም።
ሉቃስ 7፥40–47
ኢየሱስ ስለወደደችው እና በእርሱም እምነት ስለነበራት ሃጢያቶቿ ይቅር እንደተባሉላት ለሴቲቱ ነገራት። እርሱም በሰላም መሄድ እንደምትችል ነገራት።
ሉቃስ 7፥47–50