1 እና 2 ተሰሎንቄ
የብርሃን ልጆች
የኢየሱስ ክርስቶስን ምጻት እየጠበቅን በእርሱ መታመን
በጳውሎስ ጊዜ የነበሩ ቅዱሳን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ወደ ምድር የሚመጣበትን ጊዜ በማሰብ ይደሰቱ ነበር። ተሰሎንቄ በተባለ ስፍራ ውስጥ ህይወት ለቅዱሳን እየከበደ ነበር። ይህ መሆኑ ኢየሱስ በቅርቡ እንደሚመጣ የሚያሳይ መሆን አለመሆኑ ያሳስባቸው ነበር። ጳውሎስ እነርሱን ለመርዳት ደብዳቤ ጻፈላቸው።
1 ተሰሎንቄ 4፥16–18፤ 5፥1–2፤ 2 ተሰሎንቄ 1፥4
ኢየሱስ ዳግም የሚመጣበትን ቀንና ሰዓት ማንም እንደማያውቅ ጳውሎስ ተናገረ። ልክ በተኙበት ጊዜ በሌሊት ሌባ በሚመጣበት አይነት፣ ይህም ለአንዳንድ ሰዎች አስገራሚ ይሆናል።
1 ተሰሎንቄ 5፥2–3፤ 2 ተሰሎንቄ 2፥2
ነገር ግን ጳውሎስ ለቅዱሳኑ በጭለማ እንዳልሆኑ ነገራቸው። ኢየሱስ ክርስቶስን እየተከተሉ በመሆኑ ምክንያት፣ ቅዱሳን የብርሃን ልጆች ናቸው!
1 ተሰሎንቄ 5፥4–5።
ኢየሱስ ዳግም ከመምጣቱ በፊት ብዙ ሰዎች ከእውነት እንደሚያፈገፍጉ ጳውሎስ አብራርቶ ነበር። የብርሃን ልጆች የሆኑት ቅዱሳን ኢየሱስን እንዲከተሉ እና መምጣቱን እንዲጠባበቁ ይፈልግ ነበር። ይህን የምናደርግ ከሆነ፣ በአለም ምንም ይሁን ምን፣ ኢየሱስ ሲመለስ የተዘጋጀን እንሆናለን።
1 ተሰሎንቄ 1፥5፤ 2 ተሰሎንቄ 2፥3