ሉቃስ 4፥16–31
ኢየሱስ ስለ ተልዕኮው መሰከረ
በናዝሬት ተወገዘ
ኢየሱስ ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ ይኖሩ ወደነበረበት ወደ ናዝሬት ሄደ። ያም እርሱ ያደገበት ስፍራ ነበር። በሰንበትም ቀን፣ ሰዎች ሊማሩ እና እግዚአብሔርንም ሊያመልኩ ወደሚሄዱበት ወደ ምኩራብ ሄደ።
ሉቃስ 4፥16–17
በምኩራብም፣ ኢየሱስ ቆመ እናም ከነቢዩ ኢሳይያስ መጽሀፍ በመጥቀስ አነበበ። ጥቅሱም አንድ ቀን አዳኝ ይመጣል አለ። እርሱም ለድሆች ወንጌልን ይሰብካል እንዲሁም ልባቸው የተሰበሩትን ይፈውሳል። አይነ ስውሮችን እና የተጎዱትን ይረዳል።
ኢሳይያስ 61፥1–2፤ ሉቃስ 4፥17–19
ኢየሱስ ማንበቡን ጨረሰ እና ተቀመጠ። እያንዳንዱ ሰው እርሱን እየተመለከተ ነበር። በዚያ ቀን እርሱ ያነበበው ጥቅስ እውን እየተፈጸመ እንደነበር ነገራቸው። እርሱ አዳኝ ነበር።
ሉቃስ 4፥21
የናዝሬት ህዝብ ኢየሱስ በተናገረው በጣም ተደንቀው ነበር። ኢየሱስ እንዴት አዳኝ ሊሆን ይችላል? እነርሱም እርሱ የማርያም እና የዮሴፍ ልጅ ብቻ እንደነበር እንጂ የእግዜአብሔርን ልጅ እንዳልሆነ አሰቡ። ለእነርሱ፣ እርሱ ተራ ሰው የሚመስል ነበር።
ሉቃስ 4፥22
ህዝቡ እርሱ አዳኝ መሆኑን ለማረጋገጥ ተዓምራትን እንዲያደርግ እንደሚፈልጉ ኢየሱስ አወቀ። ተዓምራት ለሚያምን ህዝብ እንደሆነ እና አንዳንድ ጊዜም እግዚአብሔር የበለጠ እምነት ስላላቸው ከእስራኤል ላልሆኑት ተዓምራትን እንዳደረገላቸው አስተማረ። አንዳንዶቹ በምኩራብ የነበሩት ሰዎች በኢየሱስ ተበሳጭተው ነበር።
ሉቃስ 4፥23–28
እነርሱም ከከተማ ውጪ እስከ ኮረብታ አናት ድረስ አስገደዱት። ከኮረብታ ሊወረውሩት ፈልገው ነበር።
ሉቃስ 4፥28–29
ነገር ግን ኢየሱስ ከተበሳጩት ሰዎች አመለጠ።
ሉቃስ 4፥30
በናዝሬት ስላልፈለጉት፣ ኢየሱስ ለማስተማር ወደ ሌላ ከተማ ሄደ።
ሉቃስ 4፥31–32