ማርቆስ 2፥1–12
ኢየሱስ መራመድ የማይችልን ሰው ፈወሰ
አካላዊ እና መንፈሳዊ ፈውስ
ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ሲያስተምር ለመስማት ፈለጉ። አንድ ቀን በሰዎች በተሞላ ቤት ውስጥ ያስተምር ነበር።
ማርቆስ 2፥1–2
አራት ሰዎች መራመድ የማይችልን አንድ ጓደኛቸውን ይዘው ወደ ቤቱ መጡ። እርሱን በአልጋ ላይ መሸከም ነበረባቸው። ጓደኛቸውን ወደ ኢየሱስ ሊያመጡ ፈለጉ፣ ነገር ግን ቤቱ በሰው ተሞልቶ ስለነበር ሊገቡ አልቻሉም።
ማርቆስ 2፥3–4
በመሆኑም ጓደኛቸውን ወደ ቤቱ ጣሪያ አወጡት። የጣሪያውን ከፊሉን ከፍተው ጓደኛቸውን ከነአልጋው ወደ ቤቱ ውስጥ፣ በህዝቡም መካከል፣ በኢየሱስ ፊት አወረዱት።
ማርቆስ 2፥4
ኢየሱስም እምነታቸውንበማየት፣ መራመድ የማይችለውን ሰው፣ “ልጄ ሆይ፣ ሃጢያትህ ተሰረየችልህ” አለው።
ማርቆስ 2፥5
አንዳንድ የአይሁድ መሪዎች፣ ይህንን በሰሙ ጊዜ ተበሳጩ። ኃጢአትን ይቅር ማለት የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ አሰቡ።
ማርቆስ 2፥6–7
ነገር ግን ኢየሱስ እነርሱ ምን እንደሚያስቡ ያውቅ ነበር። እርሱ ሃጢያትን ይቅር ለማለት ሃይል እንዳለው እንዲረዱ ለመርዳት ተዓምራትን ሰራ። ሰውየውንም፣ “ተነሳ፣ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ” አለው። ሰውየውም ተነስቶ ቆመ እና ተራመደ! ሁሉም ተገረሙ እና ለእግዚአብሔርም ምስጋናን አቀረቡ።
ማርቆስ 2፥8–12