ሉቃስ 17፥11–19
ኢየሱስ ለምጽ የነበረባቸውን አስር ሰዎች ፈወሰ
የምስጋና አስፈላጊነት
ኢየሱስ እየተጓዘ እያለ በአንዲት መንደር ገባ እናም በቆዳቸው ላይ ለምጽ የተባለ በሽታ የነበረባቸውን አስር ሰዎች አየ። ሌሎች ሰዎችን በሽተኛ እንዳያደርጉ ለምጽ የነበረባቸው ሰዎች ከሌላው ህብረተሰብ፣ ከቤተሰባቸውም እንኳ፣ ራቅ ማለት ነበረባቸው።
ሉቃስ 17፧11-12
ሰዎቹ ወደ ኢየሱስ በመጣራት እንዲፈውሳቸው ጠየቁት። ኢየሱስም በከተማ ወዳሉ ካህናት እንዲሄዱ ነገራቸው። ካህናት ብቻ ነበሩ ዳግም ከህዝቡ ጋር እንዲሆኑ ሊወስኑ የሚችሉት።
ሉቃስ 17፥13-14፤ በተጨማሪ ዘሌዋውያን 14፥2-3ተመልከቱ።
አስሩ ሰዎች ወደ ካህናት እየተጓዙ እያለ ተዓምሩ ተከናወነ። ህመማቸው ተወገደ። ተፈወሱ!
ሉቃስ 17፥14
ከሰዎቹ አንዱ እንደተፈወሰ ባየ ጊዜ፣ ተመልሶ መጣ፣ በታላቅም ድምጽ እግዚአብሔርን አመሰገነ። እርሱ ሳምራዊ ነበር።
ሉቃስ 17፥15-16
እርሱም ኢየሱስ ስላደረገው ነገር በእግሩ ስር ወደቀ። ኢየሱስም የተፈወሱት ሌሎች ዘጠኙ ሰዎች ወዴት እንዳሉ ጠየቀ። አንድ ሰው ብቻ ሊያመሰግነው ተመልሶ መጣ! ኢየሱስም “ተነሣና ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል” አለው።
ሉቃስ 17፥16-19