በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ስምዖን እና የእግዚአብሔር ኃይል—ስለ እግዚአብሔር ክህነት መማር


የሐዋርያት ስራ 8፥5–24

ስምዖን እና የእግዚአብሔር ኃይል

ስለ እግዚአብሔር ክህነት መማር

ስምዖን አንድ ሐዋርያ ሰውን ሲፈውስ ተመለከተ።

ስምዖን የሚባል አንድ ሰው በሰማርያ ይኖር ነበር። የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በሰማ ጊዜ አመነ። በተጨማሪም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በእግዚአብሔር ኃይል ባደረጉት ተአምራት ተገረመ። ስምዖን ተጠመቀ፤ በሰማርያ የነበሩ ሌሎች ብዙ ወንዶችና ሴቶችም ተጠመቁ።

የሐዋርያት ስራ 8፥5–13

ጴጥሮስና ዮሐንስ እጃቸውን በሰዎቹ ራስ ላይ ጭነዋል።

በኢየሩሳሌም የነበሩት ሐዋርያት በሰማርያ የሚኖሩ ሰዎች እየተጠመቁ መሆኑን ሰሙ። ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ሰማርያ ሄዱ። የእግዚአብሔርን ኃይል ተጠቅመው በተጠመቁት ሰዎች ላይ እጃቸውን ጭነው የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ሰጧቸው።

የሐዋርያት ስራ 8፥14–17

ስምዖን የእግዚአብሔርን ክህነት ለመግዛት ገንዘብ አቀረበ።

ስምዖን ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይህን ሲያደርጉ ባየ ጊዜ ገንዘብን አቀረበላቸውና፣ “ለእኔ ደግሞ ይህን ሥልጣን ስጡኝ” አላቸው። የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ መስጠት እንዲችል የእግዚአብሔርን ክህነት መግዛት ፈለገ።

የሐዋርያት ስራ 8፥18–19

ጴጥሮስ ስምዖንን ስለ ክህነት አስተማረው።

ጴጥሮስ ማንም ሰው የእግዚአብሔርን ኃይል ሊገዛ እንደማይችል ገለጸለት። ከእርሱ የተሰጠ ስጦታ ነው። ጴጥሮስ ልቡ መለወጥ እንዳለበት ለስምዖን ነገረው። ስምዖንን ንስሐ እንዲገባና ይቅርታ እንዲጠይቅ ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልይ ጋበዘው።

የሐዋርያት ስራ 8፥20–23

ስምዖን ጴጥሮስን ይቅርታ ጠየቀው።

ስምዖን አዘነ። እርሱ እንዲለወጥ እንዲረዳው ጴጥሮስ እንዲጸልይለት ጠየቀው።

ከሐዋርያት ስራ 8፥24