የሐዋርያት ስራ 21–22፤ 26–28
በጳውሎስ የሮሜ ጉዞ ወቅት የተከሰቱ ተአምራት
ጌታ አገልጋዮቹን ይባርካል
መንፈስ ጳውሎስን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ ነገረው። በዚያ የነበሩ አያሌ ሰዎች ጳውሎስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረውን አልወደዱም ነበር። ያዙት እንዲሁም በሰንሰል አሰሩት። ጳውሎስ ከሰማይ ብርሃን ያየበትን፣ የኢየሱስን ድምጽ የሰማበትን ጊዜ እና መጠመቁንም ለሁሉም ሰው ነገረ።
የሐዋርያት ስራ 21፥4፣ 12–13፣ 27–40፤ 22፥1–16
ጳውሎስ በአስር ቤት ታሰረ፡፡ በዚያም እያለ፣ ኢየሱስ ተገለጠለት እና “ጳውሎስ ሆይ … አይዞህ” አለው። ጳውሎስ በሮሜ ስለእርሱ ምስክርነት እንደሚሰጥነገረው።
የሐዋርያት ስራ 23፥10–11
ጳውሎስ በገዢዎች እና በነገስታት ፊት እንዲቆም ተደረገ። ለእነዚህ ሃያላን ገዢዎች በድፍረት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መሰከረ። እያንዳንዱ ሰው በኢየሱስ እንዲያምን ፈለገ።
የሐዋሪያት ሥራ 24፥10–27፤ 25፥6–8፣ 17–19፤ 26፥1–29
ንጉሱም ጳውሎስ በገዢው፣ በቄሳር እንዲፈረድበት ወደ ሮ ላከው። ጳውሎስ ከሌሎች እስረኞች ጋር በመሆን በመርከብ ተጓዘ፣ በመንገዳቸውም ላይ በተለያዩ ቦታዎች ይቆሙ ነበር። በቆሙበት አንድ ቦታ፣ ጳውሎስ በቅርቡ ክረምት እንደሚሆን አወቀ። በጉዞ የሚቀጥሉ ከሆነ፣ በታላቅ አደጋ ውስጥ ይሆናሉ። እርሱም ለመርከቡ ሰራተኞች የአየር ሁኔታ እስከሚሻሻል ድረስ እንዲቆዩ ነገራቸው።
የሐዋርያት ስራ 27፥1–10
ጳውሎስን ማንም ሰው ስላላመነው ጉዟቸውን ቀጠሉ። ታላቅ ማዕበል ተነሳ፣ ለአያሌ ቀናት መርከቧ በወጀብ ተናወጠች። ጸሐይንም ሆነ ክዋክብትን ሊያዩ አልቻሉም ነበር። በማዕበሉ ምክንያት የሚሞቱ መስሏቸው ነበር።
የሐዋርያት ስራ 27፥11–20
በአንድ ሌሊት፣ መልአክ ጳውሎስን ጎበኘውና “ጳውሎስ ሆይ፣ አትፍራ” አለው። መልአኩም ጌታ ቃል እንደገባው ጳውሎስ ወደ ሮሜ በደህና እንደሚደርስ ነገረው። እርሱም ማናቸውም እንደማይሞቱ—በመርከቡ ያሉትን በሙሉ እግዚአብሔር እንደሚጠብቃቸው ተናገረ።
የሐዋርያት ስራ 27፥23–24
ጳውሎስ መልአኩ የተናገረውን ለእያንዳንዱ ሰው ነገረ። “አይዞአችሁ፣” አለ ጳውሎስ፣ “እግዚአብሔርን አምናለሁና።”
የሐዋርያት ስራ 27፥21–25
ከቀናት በኋላ፣ መርከቧ ተጋጭታ ሰመጠች። ነገር ግን ልክ መልአኩ ቃል እንደገባው፣ በመርከቧ ከነበሩ ሰዎች አንዳቸውም አልሞቱም። ሁሉም መሊታ ወደምትባል ደሴት አየዋኙ ሄዱ።
የሐዋሪያት ሥራ 27፥40–44፤ 28፥1
በመሊታ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ለጳውሎስ እና በመርከቧ ለነበሩ ለሌሎች መልካም ነበሩ። ሁሉም ሙቀት እንዲሰማቸው እሳት አነደዱ።
የሐዋሪያት ስራ 28፥2
በድንገት፣ ከእሳቱ ውስጥ አንድ እባብ ወጥቶ ጳውሎስን እጁ ላይ ነደፈው። ነገር ግን ጳውሎስ አልተጎዳም። እባቡን ከእጁ ላይ አራገፈው። ሰዎቹ በጣም ተደነቁ።
የሐዋርያት ስራ 28፥3–6
ፓብሌዎስ የተባለ ሰው ጳውሎስ በቤቱ እንዲቆይ አደረገው። የፓብሌዎስ አባት እጅግ ታሞ ነበር። ጳውሎስም እጆቹን ጫነበት እና ሊፈውሰው የእግዚአብሔርን ሃይል ተጠቀመ።
የሐዋርያት ስራ 28፥7–8
ጳውሎስ በመሊታ ለሶስት ወራት ያህል ቆየ። ጌታም በዚያ የታመሙትን እንዲባርክ እና እንዲፈውስ ብዙ ተአምራትን እንዲያደርግ ረዳው። ከዚያም፣ ልክ ጌታ ቃል እንደገባው፣ ጳውሎስ ወደ ሮሜ ተጓዘ።
የሐዋርያት ስራ 28፥9–16
ጳውሎስ ሮሜ በነበረበት ጊዜ እስረኛ ነበር። ነገር ግን ጠባቂዎቹ ሰዎች እንዲጎበኙት ይፈቅዱላቸው ነበር። ጳውሎስ ለሚሰማው ሁሉ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ያስተምር ነበር። በብዙ ስፍራ ለነበሩ የቤተክርስቲያን አባላት ደብዳቤንም ይጽፍላቸው ነበር። አንዳንዶቹ ደብዳቤዎች፣ ወይም መልእክቶች፣ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ይገኛሉ።
የሐዋርያት ስራ 28፥16–31