በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ—ህዝቡም አዳኛቸውን ተቀበሉ


ማቴዎስ 21፥1-16

ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ

ህዝቡም አዳኛቸውን ተቀበሉ

ህዝቡ ኢየሱስን ከኢየሩሳሌም ውጪ ሊያገኙት ይጠብቁታል።

ለአይሁድ አስፈላጊ የሆነው የፋሲካ በዓል ሊከበር የተቃረበበት ጊዜ ነበር። አያሌ ሰዎችም ለፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘዋል። ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱም እንዲሁ ሄደዋል። ኢየሱስ መምጣቱን ህዝቡ በሰሙ ጊዜ፣ ሊያገኙት ሄዱ።

ማቴዎስ 21፥1ዮሐንስ 12፥12-13

ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ኢየሩሳሌም እየቀረቡ ነው።

ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም በቀረቡ ጊዜ፣ አህያ ያመጡለት ዘንድ ጠየቃቸው። ከብዙ ዓመታት በፊት፣ አንድ ነቢይ አዳኝ የሆነ እርሱ በአህያ ውርንጫ ትሁት ሆኖ እንደሚመጣ ተናግሯል።

ማቴዎስ 21፥1-7፤ በተጨማሪ ዘካርያስ 9፥9ተመልከቱ።

ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።

ኢየሱስ ወደ ከተማው በአህያ ጀርባ ሆኖ ገባ። ህዝቡም ስላዩት እጅግ ተደሰቱ። እንደንጉስም ተቀበሉት። አህያይቱም ትራመድበት ዘንድ የዘንባባ ዝንጣፊ እና ልብሳቸውን በመሬት ላይ አነጠፉ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፣ “ሆሣዕና፦ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው’’ በማለት ጮኹ።

ማቴዎስ 21፥8-9ሉቃስ 19፥36-38ዮሐንስ 12፥13

ህዝቡ ኢየሱስን ይመለከታሉ።

አያሌ ህዝብም በኢየሩሳሌም የሆነው ነገር ግራ አጋብቷቸው ነበር። ‘’ይህ ማነው?’’ በማለት ጠየቁ። ሌሎችም የናዝሬቱ ኢየሱስ ነው በማለት መለሱ።

ማቴዎስ 21፥10-11

ኢየሱስ ሰዎች በቤተ መቅደሱ ውስጥ ገንዘብ ሲለዋወጡ አየ።

በመቀጠልም ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ። አንዳንድ ስዎች ገንዘብ ይለዋወጡ ነበር እና ለመስዋእት የሚሆን እንሰሳም ይገዙ ነበር። ኢየሱስ ታማኝ እንዳልሆኑ አውቋል።

ማቴዎስ 21፥12

ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ገንዘብ ሲለዋወጡ የነበሩትን ሰዎች እንዲሄዱ ነገራቸው።

ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ለአምልኮ ከመጡ ሰዎች ላይ ገንዘብ መቀበላቸውን አልወደደውም። እንዲሄዱ አደረጋቸው እናም ጠረቤዛዎቻቸውን ገለባበጠባቸው። እርሱም፣ ‘’ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል፤ ነገር ግን እናንተ የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት’’ አላቸው።

ማቴዎስ 21፥12-13፤ በተጨማሪ ኢሳያስ 56፥7ኤርሚያስ 7፥11ን ይመልከቱ።

ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ሰዎችን ፈወሰ።

አይነ ስውር የነበሩ ወይም መራመድ የተሳናቸው ሰዎች ጌታ ወዳለበት ወደ ቤተ መቅደስ መጡ፣ እናም ፈወሳቸው። ልጆችም ‘’ሆሳዕና፣’’ እርሱ አዳኝ ነው በማለት እያወደሱት ጮኹ።

ማቴዎስ 21፥14-15

ኢየሱስ ከካህናት እና ከጸሃፍት ጋር ያወራል።

አንዳንድ ካህናት እና ጸሃፍት ኢየሱስ ያደረገውን ነገር እና ልጆችም ሲናገሩ የነበረውን ነገር በሰሙ ጊዜ ተበሳጩ። እግዚአብሄር ከህጻናት አንደበት ፍጹም የሆነ ምስጋናን እንደሚያወጣ በቅዱስ መጽሀፍ የተነገረውን አስታወሳቸው።

ማቴዎስ 21፥15-16፤ በተጨማሪ መዝሙር 8፥2ተመልከቱ።