በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ጳውሎስ እና ሲላስ—ከጌታ በመጣ ተአምራት ዳኑ


የሐዋርያት ስራ 16፥9–40

ጳውሎስና ሲላስ

ከጌታ በመጣ ተአምራት ዳኑ

ጳውሎስና ሲላስ አብረው ሲጓዘ።

ጌታ ጳውሎስና ሲላስ ወንጌልን በአንድነት እንዲሰብኩ ጠራቸው። በዚያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት እንዴት እንደሚሠሩ ለማየት ወደ ብዙ ከተሞች ተጓዙ።

የሐዋሪያት ሥራ 15፥40–4116፥4–8

ጳውሎስ ራዕይን አየ።

አንድ ሌሊት ጳውሎስ በራእይ ከመቄዶንያ የመጣ አንድ ሰው ወደ ከተማው እንዲመጣ ሲለምነው አየ። ጳውሎስና ሲላስ ወዲያው ሄዱ። እግዚአብሔር እንዲሄዱ እንደሚፈልግ ያውቁ ነበር።

የሐዋርያት ስራ 16፥9–10

ጳውሎስና ሲላስ ልድያ ለምትባል ሴት ሰበኩ።

ወደ መቄዶንያ በደረሱ ጊዜ ልድያ የተባለች አንዲት ሴት ሲያስተምሩ ሰማች። ጌታ የልዲያን ልብ ከፈተ። ጳውሎስ ያስተማረውን አምና ተጠመቀች።

የሐዋርያት ስራ 16፥13–15

ልድያ ለጳውሎስና ለሲላስ በቤቷ መቆየት እንደሚችሉ ነገረቻቸው።

ልድያ ለጳውሎስና ለሲላስ በዚያ እያሉ በቤቷ ውስጥ መቆየት እንደሚችሉ ነገረቻቸው።

ከሐዋርያት ስራ 16፥15

ህዝቡ ጳውሎስንና ሲላስን ወደ ገበያ ወሰዷቸው።

ነገር ግን ጳውሎስና ሲላስ እዚያ መኖራቸውን ሁሉም አልወደዱም። አንዳንዶቹ የሚያስተምሩትን አልወደዱም። ጳውሎስንና ሲላስን ወደ ገበያ ወሰዱ እናም ለከተማይቱ አለቆች እነርሱ ሁከት እየፈጠሩ እንደሆነ ነገሯቸው።

የሐዋርያት ስራ 16፥16–21

ሕዝቡ በጳውሎስና በሲላስ ላይ ተቆጥተው ነበር።

ሕዝቡም በጳውሎስና በሲላስ ላይ ተቈጡ። የከተማይቱም አለቆች የጳውሎስንና የሲላስን ልብስ ቀደዱ እንዲሁም ሊደበድቡ ይገባል አሉ።

የሐዋርያት ስራ 16፥22–23

ጳውሎስና ሲላስ ወደ ወኅኒ ተጣሉ።

ከዚያም የከተማይቱም አለቆች ጳውሎስንና ሲላስን ወደ ወኅኒ ጣሏቸው። እግራቸውንም አስረው ዘበኛ አስቀመጡባቸው።

የሐዋርያት ስራ 16፥23–24

ጳውሎስና ሲላስ የታሰሩበት ማሰሪያ ተፈታ።

በዚያች ሌሊት ጳውሎስና ሲላስ ሌሎቹ እስረኞች እያዳምጧቸው ሳለ ለእግዚአብሔር ጸለዩ እንዲሁም መዝሙሮችን ዘመሩ። በድንገት መሬቱ መንቀጥቀጥ ጀመረ። የእስር ቤቱ በሮች ተከፈቱ፣ እስራታቸውም ተፈቱ።

የሐዋርያት ስራ 16፥25–26

ጳውሎስ ዘበኛው እንዳይጨነቅ ነገረው።

ዘበኛው ከእንቅልፉ ነቅቶ የተከፈቱትን በሮች ተመለከተ። እስረኞቹ እንዳመለጡ እና እንዲያመልጡ በመፍቀድ ችግር ውስጥ እንደሚገባ አስቦ ነበር። ጳውሎስ ዘበኛው እንዳይጨነቅ ነገረው። እስረኞቹ ሁሉ እዚያው ነበሩ።

የሐዋርያት ስራ 16፥27–28

ጳውሎስ ዘበኛው በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምን ነገረው።

ዘበኛው ፈርቶ ነበር። ጳውሎስና ሲላስ አጠገብ ተንበረከከ እናም እንዲህ አለ፣ “ለመዳን ምን ማድረግ ይገባኛል?” እነርሱም፣ “በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እመን” አሉት።

የሐዋርያት ስራ 16፥27–31

ጳውሎስና ሲላስ ወንጌልን ለዘበኛውና ለቤተሰቡ አስተማሩ።

ጳውሎስና ሲላስ ወንጌልን ለዘበኛውን እና ለቤተሰቡ አስተማሩ። ዘበኛው የጳውሎስንና የሲላስን ቁስል አከመ። በዚያች ምሽት እሱና ቤተሰቡ ተጠመቁ።

የሐዋርያት ስራ 16፥32–33