በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስ ስለ አፈር፣ ዘር፣ ዳቦ፣ እና እንቁ አስተማረ—መንፈሳዊ እውነቶችን ለመረዳት የሚያግዙን ቀላል ታሪኮች


ማቴዎስ 13

ኢየሱስ ስለ አፈር፣ ዘር፣ ዳቦ፣ እና እንቁ አስተማረ

መንፈሳዊ እውነቶችን ለመረዳት የሚያግዙን ቀላል ታሪኮች

ሰዎች እያዳመጡ ሳለ ኢየሱስ ከጀልባ ውስጥ ሆኖ ሲያስተምር።።

ኢየሱስ በአብዛኛው ጊዜ ምሳሌዎች የተባሉ ታሪኮችን ይናገር ነበር። ኢየሱስ በምሳሌዎቹም የተለመዱ የዕለት ተዕለት ነገሮችን ከወንጌሉ አስፈላጊ እውነቶች ጋር ያነጻጽር ነበር። ምሳሌዎቹንም ለመረዳት፣ ተከታዮቹ በጥንቃቄ መስማት እናም ስለ ትርጉማቸውም በጥልቀት ማሰብ ነበረባቸው። ምሳሌዎቹ እነርሱ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ለመማር ረድተዋቸዋል።

ማቴዎስ 13፥3፣ 10–15

ኢየሱስ የተወሰኑ ዘሮችን ስለዘራ አንድ ሰው በመናገር ጀመረ።

በአንድ ምሳሌም፣ አንድ ሰው የተወሰኑ ዘሮችን ሊዘራ ወደ እርሻ ሄደ። በእርሻውም ውስጥ ብዙ ዘሮችን አሰራጨ። ዘሮቹም በተለያየ የመሬት አይነት ላይ ወደቁ።

ማቴዎስ 13፥3

የተወሰኑት ዘሮች በደረቀ የአቧራ መንገድ ላይ ወደቁ።

የተወሰኑት ዘሮች በፍጹም ሊያድጉ ከማይችሉበት በደረቀ የአቧራ መንገድ ላይ ወደቁ። በዚያም የወደቁትን ዘሮች ወፎች መጥተው በሏቸው።

ማቴዎስ 13፥4

የተወሰኑት ዘሮች በአለታማ አፈር ላይ ወደቁ።

የተወሰኑት ዘሮች በአለታማ አፈር ላይ ወደቁ። ዘሮቹ በፍጥነት አቆጠቆጡ፣ ነገር ግን በአለቱ ምክንያት ስሮቹ ሊያድጉ አልቻሉም። ሙቀትም በሆነ ጊዜ፣ እጽዋቶቹ ደረቁ።

ማቴዎስ 13፥5–6

የተወሰኑት ዘሮች አረም በሞላበት አፈር ላይ ወደቁ።

አንዳንዶቹም ዘሮች እሾሃማ አረም በሞላበት አፈር ላይ ወደቁ። በእሾሃማ አረሙ ምክንያት፣ ዘሮቹ ሊያድጉ አልቻሉም።

ማቴዎስ 13፥7

የተወሰኑት ዘሮች ጠንካራ እጽዋት በመሆን አደጉ።

የተወሰኑት ዘሮች በመልካም መሬት ላይ ወደቁ። እነርሱም ጠንካራ፣ ጤናማ እጽዋት ሆኑ። ብዙ ፍሬም አፈሩ።

ማቴዎስ 13፥8

ኢየሱስ ዘሮቹ እንደእግዚአብሔር ቃል መሆናቸውን ገለጸ።

ደቀ መዛሙርቱ እንዲገባቸው ለመርዳት፣ ኢየሱስ ምሳሌው ምን ማለት እንደሆነ አብራራላቸው። ዘሮቹም እንደእግዚአብሔር ቃላት ናቸው። የተለያዩት የአፈር አይነቶችም የሰዎችን ልብ የሚወክል እና የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት የሚያሳዩት የተለያዩ መንገዶች ናቸው። መልካሙ አፈር የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰሙትን፣ የሚረዱትን፣ እና እርሱንም የሚታዘዙትን ይወክላል።

ማቴዎስ 13፥18–23

ኢየሱስ ስለ ሰናፍጭ ዘር ያስተምራል።

የእግዚአብሔር መንግስት እንዴት እንደሚያድግ ለማስተማር፣ ኢየሱስ ስለ ሰናፍጭ ዘር ተናገረ። ይህች በጣም ትንሽ ነች፣ ነገር ግን ወፎች ሊኖሩባት እስከሚችሉ ድረስ ዛፍ በመሆን ታድጋለች።

ማቴዎስ 13፥31–32

ኢየሱስ ስለ ዳቦ እና እርሾ ያስተምራል።

ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንግስት ሴት ዳቦ ለመጋገር የተጠቀመችውን እርሾ እንደሚመስልም ጭምር ተናገረ። አንድን ሙሉ ዳቦ ለመጋገር ጥቂት እርሾ ብቻ ያስፈልጋል።

ማቴዎስ 13፥33

ኢየሱስ ስለ እንቁ ምሳሌን ተናገረ።

ኢየሱስ እንቁን ገዝቶ ስለነበር አንድ ሰው ሌላ ታሪክን ተናገረ። በጣም ያማረ እና ጠቃሚ የሆነን አንድ እንቁ አገኘ። እንቁውንም ይገዛ ዘንድ ያለውን ሁሉ ሸጠ። ኢየሱስ የወንጌል በረከቶች በጣም ዋጋ ያላቸው በመሆናቸው ልናገኛቸው ማድረግ ያለብንን ሁሉ እንድናደርግ ለማስተማር ኢየሱስ ይህንን ታሪክ ተናገረ።

ማቴዎስ 13፥45–46