በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
እስጢፋኖስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መሰከረ—ደፋር አገልጋይ ለምስክርነቱ ሕይወቱን አሳልፎ ሰጠ


የሐዋሪያት ሥራ 6–7

እስጢፋኖስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መሰከረ

ደፋር አገልጋይ ለምስክርነቱ ሕይወቱን አሳልፎ ሰጠ

ሁለት ሐዋርያት ከኢየሱስ ቤተክርስቲያን አባላት ጋር።

ቤተክርስቲያኗ በፍጥነት እያደገች ነበር። ሁሉንም አባላት ለመንከባከብ ለሐዋርያቱ አስቸጋሪ እየሆነ መጣ።

የሐዋርያት ስራ 6፥1–2

አንድ ሐዋርያ እስጢፋኖስን የክህነት በረከት ሰጠው።

ሐዋርያትም ሊረዱ የሚችሉ ሰባት ሰዎችን ለመጥራት ወሰኑ። እነርሱም ጥበበኞችና መንፈስ ቅዱስ የተሞሉ ሰዎችን እንዲፈልጉ አባላትን ጠየቁ።

የሐዋሪያት ስራ 6፥3

እስጢፋኖስ አንድን ሰው ሲፈውስ።

ከተመረጡት ሰዎች አንዱ እስጢፋኖስ ነበር። ሐዋርያትም ቡራኬን ሰጡት። እስጢፋኖስ ብዙ እምነት ነበረው እናም በሕዝቡ መካከል ታላላቅ ተአምራትን አደረገ።

የሐዋርያት ስራ 6፥5–8

እስጢፋኖስም ከሊቀ ካህናቱና ከሌሎች መሪዎች ጋር ተነጋገረ።

እስጢፋኖስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በጥበብና በመንፈስ አስተማረ። የምኩራብ አለቆች ግን ያስተምረውን ነገር አልወደዱትም። ሙሴንና እግዚአብሔርን ተሳድቧል አሉት። እስጢፋኖስን በሊቀ ካህናቱና በሌሎች መሪዎች ፊት አመጡት።

የሐዋሪያት ሥራ 6፥9–157፥1

እስጢፋኖስ መሪዎቹን ስለ ኢየሱስ አስተማረ።

የእስጢፋኖስ ፊት የመልአክ ፊት ይመስል ነበር። እስራኤልን ለማዳን እግዚአብሔር ሙሴን እንደላከ፣ ነገር ግን ሕዝቡ ሙሴን ሁልጊዜ እንደዳልተከተለው ለመሪዎቹ አስተውሳቸው። እስጢፋኖስ ሙሴ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ተናገረ። እግዚአብሔር ሕዝቡን እንዲያድን ኢየሱስን ላከ፣ ቢሆንም መሪዎቹ ግን አልተከተሉትም። መሪዎቹም በእስጢፋኖስ ላይ ተናደዱ።

የሐዋርያት ስራ 7፥20–43፣ 51–54

እስጢፋኖስ የሰማይ አባትና የኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ አየ።

እስጢፋኖስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ወደ ሰማይ ተመለከተ። ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ አባት አጠገብ ቆሞ አየ።

የሐዋርያት ስራ 7፥55–56

መሪዎቹ እስጢፋኖስን ያዙት።

እስጢፋኖስ ያየውን ለመሪዎቹ ሲነግራቸው የበለጠ ተበሳጩ። እነርሱም በቁጣ ጮኹ እና እስጢፋኖስን ያዙት። ከዚያም እርሱን ከከተማይቱ ጎትተው አውጥተው ወሰዱት።

ከሐዋርያት ስራ 7፥57

ሳኦል የእስጢፋኖስን ሞት እየተመለከተ።

ሳኦል በሚሉት በአንድ ሰው እግር አጠገብ ልብሳቸውን ጣሉ። እስጢፋኖስን ሊገድሉት ድንጋይ ወረወሩበት። ሳኦልም በሚያደርጉት ነገር ተስማማ። እስጢፋኖስ ጸለየ። የጎዱትን ሰዎች ይቅር እንዲላቸውም ጌታን ጠየቀ። በተጨማሪም ጌታ መንፈሱን ወደ ሰማይ እንዲቀበለው ጠየቀ።

የሐዋሪያት ሥራ 7፥59–608፥1