በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
የአስሩ ቆነጃጅት ምሳሌ—ለኢየሱስ ዳግም ምፅዓት መዘጋጀት


ማቴዎስ 25፥1–13

የአስርቱ ቆነጃጅት ምሳሌ

ለኢየሱስ ዳግም ምፅዓት መዘጋጀት

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መቼ እንደሚመለስ ጠየቁት።

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ወደ አባቱ ከተመለሰ በኋላ አንድ ቀን ወደ ምድር እንደገና እንደሚመጣ ያውቁ ነበር። መቼ ተመልሶ እንደሚመጣ እንዴት ማወቅ እንደሚችሉ ጠየቁት። ለመመለሱ ለመዘጋጀት ፈልገው ነበር። እነርሱን ለመመለስ፣ ኢየሱስ ምሳሌ ተናገረ።

ማቴዎስ 24፥3

አስር ሴቶች ወደ ሰርግ ይሄዳሉ።

በምሳሌው ውስጥ፣ አስር ሴቶች ወደ ሰርግ እየሄዱ ነበር። ሰርጉ በምሽት ነበር፣ ስለዚህ ሴቶቹ በመንገዳቸው ብርሀን ለማግኘት በዘይት የተሞሉ መብራቶች መያዝ ነበረባቸው። አምስቱ ሴቶች ጥበበኛ ነበሩ እና ብቁ የሚሆን ዘይት ያዙ። ሌሎቹ አምስቶች ሞኞች ነበሩ እናም በቂ ዘይት አልያዙም።

ማቴዎስ 25፥1–4

ሴቶቹ ሙሽራውን እየጠበቁ አንቅልፍ ወሰዳቸው።

ሴቶቹ ሙሽራው እና ሚዜዎቹ እስከሚመጡ ድረስ መጠበቅ ነበረባቸው። ነገር ግን ሙሽራው ዘገየ። እየጠበቁ ሳሉ፣ ሁሉም አንቀላፉ።

ማቴዎስ 25፥5

አንድ ሰው ሙሽራው በመጨረሻ እየመጣ ነው አለ።

እኩለ ሌሊትም ሲሆን፣ አንድ ሰው ሙሽራው በመጨረሻ እየመጣ ነው ብለው ጮሁ። ሴቶቹ ከሚዜዎቹ ጋር የሚቀላቀሉበት ጊዜ አሁን ነበር።

ማቴዎስ 25፥6

አምስት ሴቶች መብራታቸውን ማዘጋጀት ቻሉ። ሌሎቹ አምስት ሴቶች ግን ምንም ዘይት አልነበራቸውም።

ሁሉም ሴቶች መንገዳቸውን ለማብራት መብራታቸውን አነሱ። ብቁ ዘይት ያላመጡት አምስት ሴቶች ግን ምንም ብርሀን አልነበራቸውም። ሙሽራውን እየጠበቁ ሳሉ ዘይቱን በመጠቀም ጨርሰው ነበር።

ማቴዎስ 25፥7–8

ዘይት የሌላቸው ሰዎች ተጨማሪ ለመግዛት ሄዱ።

ዘይት የሌላቸው አምስት ሴቶች ሌሎቹ ያላቸውን እንዲያካፍሏቸው ጠየቁ። ነገር ግን ለመካፈል ብቁ ዘይት አልነበረም። ዘይት የሌላቸው አምስት ሴቶች ተጨማሪ ለመግዛት በፍጥነት ሄዱ።

ማቴዎስ 25፥8–9

ሙሽራው መጣና ተዘጋጅተው የነበሩትን አምስት ሴቶች አነጋገረ።

እነርሱ ሄደው ሳለ፣ ሙሽራው መጣ! ተዘጋጅተው የነበሩት አምስቱ ሴቶች ወደ ሰርጉ ከእርሱ ጋር ሄዱ።

ማቴዎስ 25፥10

ዘይት ለመግዛት የሄዱት ሴቶች ወደ ሰርጉ መሄድ አልቻሉም።

ሌሎቹ ሴቶች ሲመለሱ፣ በሩ ተዘግቶ ነበር። በሩን አንኳኩ እናም ሙሽራው እንዲያስገባቸው ጠየቁት። ነገር ግን ጊዜው ረፍዶ ነበር። ወደ ሰርጉ መግባት አልቻሉም።

ማቴዎስ 25፥11–12

ኢየሱስ በሚመለስበት ጊዜ እንዲዘጋጁ ተከታዮቹን አስተማረ።

ኢየሱስ በምሳሌ ውስጥ እንደነበረው ሙሽራ ነው። ማንም ሰው መቼ ዳግም እንደሚመለስ አያውቅም። የሰማይ አባት ብቻ ነው ያን የሚያውቀው። ስለዚህ ተከታዮቹ ልክ ብቁ ዘይት እንዳላቸው ሴቶች የተዘጋጁ እንዲሆኑ ኢየሱስ ነገራቸው። የጌታን ትእዛዛት የሚያከብሩ እና መንፈስን የሚከተሉ ሰዎች፣ ኢየሱስ ዳግም በሚመለስበት ጊዜ ዝግጁ ይሆናሉ።

ማቴዎስ 24፥3625፥13ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥56–57