በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
በእምነት አንድነት—ኢየሱስ ክርስቶስ በህይወት በሚኖሩ ሐዋርያት እና ነቢያት ቤተክርስቲያኑን ይመራል


ኤፌሶን 2፥19–204፥11–14

በእምነት አንድነት

ኢየሱስ ክርስቶስ በህይወት በሚኖሩ ሐዋርያት እና ነቢያት ቤተክርስቲያኑን ይመራል።

ጳውሎስ እና ሌሎች ሐዋርያት አዲስ የቤተክርስቲያን አባላትን እያጠመቁ እና እያረጋገጡ።

የኢየሱስሐዋርያት የእርሱን ወንጌል በብዙ አገራት ሰበኩ። ወንጌሉን ያመኑ ሰዎችም ተጠምቀው ነበር። ምንም እንኳ ከተለያየ ስፍራ ቢመጡም፣ እያንዳንዱ ሰው በአዳኙ ቤተክርስቲያን ተቀባይነት እንዳለው እንዲሰማው ሐዋርያው ጳውሎስ ይፈልግ ነበር።

ማቴዎስ 28፥19–20ኤፌሶን 2፥19

ኢየሱስ በዙሪያው ህዝብ ከበውት።

ጳውሎስ በኤፌሶን ለነበሩ ቅዱሳን ደብዳቤ ጻፈላቸው። እርሱም ኢየሱስ ለእኛ በሞተ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን ልጆች የሚለያይ ግድግዳ ፈርሷል አለ። እነርሱ ከየትም ቢመጡ፣ ከዚህ በኋላ እንግዶች አይደሉም። ወንጌልን ለመቀበል እና እንደ አንድ ትልቅ ቤተሰብ “የእግዚአብሔር ቤት” አካል ለመሆን ይችላሉ።

ኤፌሶን 2፥11–19

ኢየሱስ ከፊት ለፊቱ የህንጻ የማዕዘን ድንጋይ እያለ፣ ልጆችን በቡድን ሲያስተምር።

ቤተክርስቲያን እንደ ጠንካራ ህንጻ እንደሆነች ጳውሎስ አስተማረ። ህንጻው ጽኑ መሰረት ይፈልጋል። በመሰረቱ ላይ እጅግ አስፈላጊው ድንጋይ የማእዘን ድንጋይ ነው። የቀሩት ሁሉም ድንጋዮች በማእዘኑ ድንጋይ ላይ ይሰራሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ የቤተክርስቲያኗ የማዕዘን ድንጋይ ነው።

ኤፌሶን 2፥20

እያስተማሩ፣ እያገለገሉ፣ እና ወንጌሉን እያካፈሉ ያሉ ሰዎች ምስል።

የቀሩት የቤተክርስቲያኗ መሰረቶች የኢየሱስ ክርስቶስን ምስክርነት የያዙት ነቢያት እና ሐዋርያት ናቸው። ጌታ በተጨማሪ ሁላችንም በማስተማር፣ በማገልገል፣ ወንጌልን በማካፈል እና በተለያዩ መንገዶች ቤተክርስቲያኑን እንድንገነባ ጋብዞናል።

ኤፌሶን 2፥204፥11–12

በቡድን ያሉ ልጆች ባጋራ አንድነት ሲሆኑ።

ጳውሎስ እንዳለው እያንዳንዱ ሰው ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲያውቅ ለመርዳት ቤተክርስቲያን ታስፈልጋለች። የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም በነቢያቱና በሐዋርያቱ ጽኑ መሰረት አማካይነት ዛሬ በምድር ላይ አለች። በእርሱ ቤተክርስቲያን አማካይነት፣ “በእምነት አንድነት” ማደግና ይበልጥ እንደ ኢየሱስ መሆን እንችላለን።

ኤፌሶን 2፥21–224፥13