በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስና ሀብታሙ ወጣት —“የዘላለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ?”


ማርቆስ 10፥17–31

ኢየሱስና ሀብታሙ ወጣት

“የዘላለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ?”

አንድ ወጣት ሰው ወደ ኢየሱስ ሲሮጥ።

ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ በመንገድ ላይ እያሉ፣ አንድ ሀብታም ወጣት ሰው ወደ ኢየሱስ ሮጦ በፊቱ ተንበረከከ። ከሰማይ አባት ጋር እንደገና ለመኖር ምን ማድረግ እንደሚገባው ኢየሱስን ጠየቀ።

ማርቆስ 10፥17

ኢየሱስ ወጣቱን ሰው ስለ ትእዛዛት እንዲያስታውስ አደረገው።

ኢየሱስ ወጣቱ ሰው ስለ እግዚአብሔር ትእዛዛት እንደሚያውቅ አስታወሰው፦ አትግደል፣ አትዋሽ ወይም አትስረቅ፣ እንዲሁም አባት እና እናትህን አክብር።

ማርቆስ 10፥19

ወጣቱም ሰው ለኢየሱስ መለሰ።

ወጣቱም ሰው እነዚህን ትእዛዛት ከልጅነቱ ጀምሮ ያከብራቸው እንደነበር መልስ ሰጠ።

ማርቆስ 10፥20

ኢየሱስ ወጣቱን ሰው አስተማረው።

ኢየሱስ ወጣቱን ሰው በፍቅር ተመለከተው። አንድ ተጨማሪ ነገር ማድረግ እንዳለበት ነገረው። ያለውን ነገሮች በሙሉ መሸጥ፣ ገንዘቡን ለድሆች መስጠት፣ እና ከኢየሱስ ተከታዮች አንዱ መሆን ያስፈልገው ነበር። ከዚያም የሰማይ ሀብቶች ይኖሩታል።

ማርቆስ 10፥21

ወጣቱ ዞር ብሎ ሄደ።

ወጣቱ በጣም ሀብታ ነበር። ያልወን ነገሮች ሁሉ ለመስጠት አልፈለገም። አዝኖም ሄደ።

ማርቆስ 10፥22

ኢየሱስ ሀብቶችን ሳይሆን እግዚአብሔርን ማመን እንዳለብን ገለጸ።

ኢየሱስም ሀብትን የሚወዱ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከመግባት ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል አለ። ደቀመዛሙርቱ ተገርምመው ነበር። “እንግዲያ ማን ሊድን ይችላል?” ብለው ጠየቁ። ኢየሱስ ለመዳን እግዚአብሔርን ማመን እንዳለብን ገለጸ። እርሱም “በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ይቻላልና” አለ።

ማርቆስ 10፥23–30