በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ—እግዚአብሔር ለኤልሳቤጥ እና ለዘካርያስ የገባውን ቃል ጠበቀ


ሉቃስ 1፥5–25፣ 57–80

መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ

እግዚአብሔር ለኤልሳቤጥ እና ለዘካርያስ የገባውን ቃል ጠበቀ

ዘካርያስ እና ኤልሳቤጥ ልጅ እንዲኖራቸው ሲጽልዩ።

ዘካርያስ እና ኤልሳቤጥ እግዚአብሔርን ይወዱ የነበሩ ታማኝ ሰዎች ነበሩ። ልጅን ለማግኘት ጸለዩ። አሁን እነርሱ በጣም አርጅተው ነበር፣ እናም እስካሁንም ልጆች አልነበሯቸውም።

ሉቃስ 1፥5–7

ዘካርያስ በቤተመቅደስ ሲያገለግል።

ዘካርያስ በኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ውስጥ ያገለግል የነበረ ካህን ነበር። አንድ ቀን፣ በቤተመቅደስ የተቀደሰ ክፍል ውስጥ እጣን እንዲያጨስ ተመረጠ።

ሉቃስ 1፥8–10

መልአክ ለዘካርያስ ሲገለጥ።

በድንገትም አንድ መልአክ ተገለጠ። ዘካርያስ ፈርቶ ነበር። መልአኩም፣ “ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ” አለው። እርሱም ዘካርያስ እና ኤልሳቤጥ ልጅ እንደሚወልዱ ተናገረ። ስሙንም ዮሐንስ ብለው ይጠሩታል። መልአኩም ዮሐንስ የሚሰራው አስፈላጊ የሆነ ስራ እንዳለውም ተናገረ። አዳኙ ሲመጣ ሰዎች እርሱን ለመቀበል እንዲዘጋጁ ይረዳል።

ሉቃስ 1፥12–17

ዘካርያስ ከመልአኩ ጋር እየተነጋገረ።

ዘካርያስ መልአኩ እየተናገረ ያለውን ማመን አልቻለም። እርሱም ሆነ ኤልሳቤጥ ልጆች ለመውለድ ለመቻል እጅግ አርጅተ ነበር። መልአኩም ዘካርያስ የእርሱን መልዕክት ባለማመኑ ምክንያት ዮሐንስ እስከሚወለድ ድረስ መናገር እንደማይችል ተናገረ።

ሉቃስ 1፥18–20

ዘካርያስ ከቤተመቅደስ ሲወጣ። እርሱ መናገር አልቻለም።

ዘካርያስ በቤተመቅደስ ውስጥ ለምን ብዙ ጊዜ እንደቆየ ህዝቡ ግራ ተጋብተው ነበር። እርሱ በወጣ ጊዜ መናገር አልቻለም። አንድ የተለየ ነገር እንደተከናወነ ገመቱ።

ሉቃስ 1፥12–23

ዘካርያስ እና ኤልሳቤጥ አዲሱን ህጻን አቅፈው።

ከወራት በኋላ፣ ልክ መልአኩ ቃል እንደገባው ኤልሳቤጥ ልጅ ወለደች። ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞቻቸው በጣም ተደሰቱ! ልጁን ለማግኘት መጡ።

ሉቃስ 1፥57–59

ኤልሳቤጥ እና ዘካርያስ ለህጻኑ አዲስ ስም ሲሰጡ።

ልጁ ልክ እንደአባቱ ዘካርያስ ተብሎ መሰየም ያለበት መስሏቸው ነበር። ኤልሳቤጥም፣ “ዮሐንስ ይባል እንጂ” አለች። አሁንም መናገር ያልቻለውን ዘካርያስን ጠየቁት። “ስሙ ዮሐንስ ነው” በማለት ጻፈ። ሁሉም ተገረሙ።

ሉቃስ 1፥59–63

ዘካርያስም ህጻኑ ነቢይ እንደሚሆን ተናገረ።

በድንገት፣ ዘካርያስ መናገር ቻለ። እግዚአብሔርን አመሰገነ እና በመንፈስ ቅዱስም ተሞላ። እግዚአብሔርም ለህዝቡ ቃል ኪዳኑን እንዳስታወሰ ለሁሉም ሰው ተናገረ። ዮሐንስም ነቢይ እንደሚሆን ተናገረ። ዮሐንስ ሰዎችን ንስሐ እንዲገቡ እና እንዲጠመቁ ያስተምራቸዋል። ከኢየሱስ ክርስቶስ ለመማር ዝግጁ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል።

ሉቃስ 1፥64–80