ዕብራውያን 11–12
በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት መኖር
እርሱ “የእምነታችን ጀማሪ እና ፈጻሚ” ነው
በቀድሞዋ ቤተክርስቲያን ውስጥ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ መሆን ሁልጊዜ ቀላል አልነበረም። አንዳንድ ጊዜ በእምነታቸው ምክንያት ሰዎች የቤተክርስቲያን አባላትን ይጠሏቸው ወይም ይሳለቁባቸው ነበር። ጳውሎስ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እምነታቸውን እንዲጠብቁ ሊረዳቸው ይፈልግ ነበር።
ዕብራውያን 10፥32–39
ጳውሎስ ለዕብራውያን፣ ወይም ለአይሁድ፣ ቅዱሳን ደብዳቤ ጻፈላቸው። እምነት ማለት ምንም እንኳ ልናየው ባንችልም በአንድ ነገር ማመን ወይም ተሳፋ ማድረግ እንደሆነ አስተማረ። ለምሳሌ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ማለት ተስፋ ያደረግናቸውን በረከቶች ባንቀበልም እንኳ እርሱን እና የተስፋ ቃሉን ማመን ማለት ነው።
ዕብራውያን 11፥1፣ 6
የዕብራውያን ቅዱሳን ፈተናዎቻቸውን በእምነት እንዲወጡ ለመርዳት፣ ጳውሎስ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ታላቅ እምነት ስለነበራቸው ሰዎች አስታወሳቸው።
ዕብራውያን 11፥4–40
ለምሳሌ፣ ጳውሎስ ስለኖህ ተናገረ። እግዚአብሔር ኖህ ቤተሰቡን ከጎርፍ ለማዳን መርከብ መስራት እንዳለበት ነግሮት ነበር። ኖህ ዝናብን ከማየቱ በፊት እንኳ ለመታዘዝ እምነት ነበረው።
ዕብራውያን 11፥7
እግዚአብሔር ወደ ተሻለ ስፍራ እንደሚመራቸው ቃል ስለገባላቸው ስለአብርሃም እና ሳራ ጳውሎስ ተናገረ። ምንም ያረጁ ቢሆን እና ልጆች ባይኖሯቸውም፣ ታላቅ ቤተሰብ እንደሚኖራቸው እግዚአብሔር የሰጣቸውን የተስፋ ቃል እንዲሁ አምነዋል።
ዕብራውያን 11፥8–16
ጳውሎስ ስለሙሴ እናት፣ ስለ አያቤድ እንዲሁ ተናግሯል። እርሱ ህጻን እያለ ክፉ ከሆነው ንጉስ ልትጠብቀው ለመደበቅ እምነት ነበራት።
ዕብራውያን 11፥23
ሙሴ ግብጽ ውስጥ አደገ። ባለጠጋ እና የተመቸው መሆን ይችል ነበር። ነገር ግን በእግዚአብሔር እና በበረከቱ ላይ እምነት ስለነበረው ያንን ሁሉ ተወ።
ዕብራውያን 11፥24–27
በእምነቱ ምክንያት ሙሴ የእግዚአብሔርን ህዝብ ከባርነት ሊያወጣ ችሏል። እነርሱ በቀይ ባሕር በኩል በደረቅ መሬት ተራምደው ተሻግረዋል።
ዕብራውያን 11፥29
ጳውሎስ ስለረዓብም እንዲሁ ተናግሯል። በከተማዋ ውስጥ ሌላ ማንም ጌታን ባላመነበት ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን ህዝብ ለመርዳት እምነት ነበራት። እምነቷ ቤተሰቧን አድኗል።
ዕብራውያን 11፥30–31
ህይወት ከባድ ቢሆንም፣ እነዚህ አያሌ የእምነት ምሳሌዎች በኢየሱስ ክርስቶስ እንድናምን ሊረዱን እንደሚችሉ ጳውሎስ ተናግሯል። ንሰሃ ልንገባ እና “የእምነታችን ጀማሪ እና ፈጻሚ” የሆነውን ኢየሱስን መመልከት እንችላለን። የሃጢያት ክፍያው ታላቅ ደስታ እና ፈውስ እንደሚያመጣልን ስላወቀ ለእኛ ለመሞት ፈቃደኛ ነበር!
ዕብራውያን 12፥1–2