በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
የመክሊት ምሳሌ—እግዚአብሔር የሰጠንን ነገር በአግባቡ መጠቀም


ማቴዎስ 25፥14–30

የመክሊት ምሳሌ

የመክሊት ምሳሌ—እግዚአብሔር የሰጠንን ነገር በአግባቡ መጠቀም

ኢየሱስ ስለአንድ ሰው እና ስለአገልጋዮቹ ምሳሌ ተናገረ።

ስለእግዚአብሔር መንግስት ለማስተማር፣ ኢየሱስ ምሳሌን ተናገረ። በምሳሌው ውስጥ፣ አንድ ሰው ወደ ሩቅ አገር ለመጓዝ እየተዘጋጀ ነበር። ከመሄዱ በፊት፣ ከአገልጋዮቹ መካከል ከሶስቱ ጋር ተገናኘና በጎዞ ላይ ሳለ ገንዘቡን እንዲጠብቁለት ጠየቃቸው።

ማቴዎስ 25፥14

ሰውየው ለእያንዳንዱ አገልጋዮቹ መክሊት ሰጣቸው።

ሰውየው ለእያንዳንዱ አገልጋዮቹ መክሊት ተብሎ የሚጠራ ብዙ ገንዘብ ሰጣቸው። ለአንዱ አገልጋይ አምስት መክሊት ሰጠ። ለሌላው አገልጋይ ሁለት መክሊት ሰጠ። እንዲሁም ለመጨረሻው አገልጋይ አንድ መክሊት ሰጠ። ከዚያም ወደጉዞው ሄደ።

ማቴዎስ 25፥15

አንዱ አገልጋይ አምስት ተጨማሪ መክሊት አገኘ።

አምስት መክሊት የተቀበለው አገልጋይ ጠንክሮ ሰራ። መክሊቱን በመጠቀም ተጨማሪ አምስት ትርፍ መክሊት አገኘ።

ማቴዎስ 25፥16

አንዱ አገልጋይ ሁለት ተጨማሪ መክሊት አገኘ።

አምስት መክሊት የተቀበለው አገልጋይ ጠንክሮ ሰራ። መክሊቱን በመጠቀም ተጨማሪ ሁለት ትርፍ መክሊት አገኘ።

ማቴዎስ 25፥17

አንዱ አገልጋይ መክሊቱን ቀበረ።

አንድ መክሊት የተቀበለው አገልጋይ ምድርን ቈፈረና መክሊቱን ቀበረ።

የማቴዎስ 25፥18

ሰውየው ከጉዞው ተመለሰ።

ከጊዜ በኋላ ሰውየው ከጉዞው ተመለሰ። አገልጋዮቹ በሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩ ለማወቅ ፈለገ።

ማቴዎስ 25፥19

ሰውየው በሁለቱ አገልጋዮች ተደሰተ።

አምስት መክሊት የተቀበለው አገልጋይ እና ሁለት መክሊት የተቀበለው አገልጋይ ጌታቸው በጉዞ ላይ እንዳለ እንዴት ሁለት እጥፍ ትርፍ እንዳገኙ ነገሩት። ጌታውም ተደሰተ። ታማኝ ስለነበሩ ይበልጥ በብዙ ነገር ላይ ሀላፊ እንዲሆኑ እንደሚያምናቸው ነገራቸው። ደስተኛ እንዲሆኑ ነገራቸው።

ማቴዎስ 25፥20–23

ሶስተኛው አገልጋይ መክሊቱን ደብቄዋለሁ አለ።

አንድ መክሊት የተቀበለው አገልጋይ ፈርቶ እንደነበረ፣ ስለዚህ መክሊቱን በምድር እንደደበቀው ለጌታው ነገረ። መክሊቱን ለጌታው መለሰ።

ማቴዎስ 25፥24–25

ሰውየው በአገልጋዩ አልተደሰተም።

ጌታው በአገልጋዩ አልተደሰተም ነበር። አገልጋዩ የተሰጠውን ተጠቅሞ ተጨማሪ መክሊቶችን ማትረፍ ነበረበት አለው። ጌታውም መክሊቱን አሥር መክሊት ላለው አገልጋይ ሰጠው። ጌታው አገልጋዮቹ የሰጣቸውን መክሊት ተጠቅመው መንግሥቱን እንዲገነቡ ፈልጎ ነበር።

ማቴዎስ 25፥26–29