ማቴዎስ 1፤ ሉቃስ 1
መላእክት ማርያምን እና ዮሴፍን ጎብኙ
የእግዜአብሔርን ልጅ ለመጠበቅ መመረጥ
ማርያም የተባለች አንዲት ሴት በናዝሬት ከተማ ውስጥ ትኖር ነበር። እግዚአብሔርን የምትወድ እና ትእዛዛቱንም የምታከብር ነበረች። ማርያምም እርሱም እንዲሁ እግዚአብሔርን ይወደ የነበረ ዮሴፍ የተባለን ሰው ልታገባ ነበር።
ማቴዎስ 1፥18–19፤ ሉቃስ 1፥26–28
አንድ ቀን፣ ገብርኤል የተባለ መልአክ ማርያምን ጎበኛት። በመጀመሪያ ማርያም ፈርታ ነበር። ነገር ግን ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ መሆኑን ተናገረ። ማርያም መፍራት አልነበረባትም። እርሱም ማርያም ለእግዚአብሔር እጅግ ልዩ እንደሆነች እና በቅርቡም ልጅ እንደምትወልድ ተናገረ። የማርያም ልጅ የእግዚአብሔር ልጅ፣ ኢየሱስ ይሆናል።
ሉቃስ 1፥26–33
ነገር ግን ማርያም ግራ ታጋብታ ነበር። ከዮሴፍ ጋር ገና አልተጋባችም ነበር። እንዴት ልጅ ልትወልድ ትችላለች? ገብረኤልም ይህ በእግዚአብሔር ሃይል እንደሚከሰት አብራራ። “ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና” ብሎ ነገራት።
ሉቃስ 1፥34–37
ማርያም ትሁት እና ታማኝ ነበረች። እርሷ ለገብረኤል የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደሆነች ተናገረች። እርሷ የእግዚአብሔር ልጅ እናት ለመሆን ፈቃደኛ ነበረች።
ሉቃስ 1፥38
ዮሴፍ፣ ማርያም ልጅ እንደምትወልድ ባወቀ ጊዜ ተረበሸ። አሁንም ማርያምን ማግባት እንዳለበት አሰበ።
ማቴዎስ 1፥19
ነገር ግን በአንድ ሌሊት በህልሙ አንድ መልአክ ለዮሴፍ ተገለጠ። መልአኩም የማርያም ልጅ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እና ስሙንም ኢየሱስ ብሎ ሊሰይመው እንደሚገባ ለዮሴፍ ነገረው። ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ከሃጢያታቸው ያድናቸዋል። መልአኩ አሁንም ዮሴፍ ማርያምን ማግባት እንዳለበት ተናገረ።
ማቴዎስ 1፥20–23
ዮሴፍ መልአኩ እንደነገረው አደረገ። ማርያም እና ዮሴፍ ተጋቡ።
ማቴዎስ 1፥24።
ማርያም ዘመዷን ኤልሳቤጥን ለመጎብኘት ሄደች። መልአኩ ለማርያም ኤልሳቤጥ ምንም እንኳን በጣም ያረጀች ብትሆንም እርጉዝ መሆኗን ጭምር ነገራት። ይህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሌላው ተዓምር ነበር። ልጇም መጥምቁ ዮሐንስ ለመሆን ያድጋል። ማርያም ወደ ቤቱ ስትገባ፣ ለኤልሳቤጥ ሰላምታ ሰጠቻት።
ሉቃስ 1፧13–17፣ 36፣ 39–40
ኤልሳቤጥ የማርያምን ድምጽ እንደሰማች፣ የኤልሳቤት ልጅ በውስጧ በደስታ ዘለለ። ኤልሳቤጥ በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች። ማርያም የእግዚአብሔርን ልጅ እንደጸነሰች አወቀች። ማርያም ከኤልሳቤጥ ጋር ተደሰተች። እርሱ ልጆቹን ለመባረክ እያደረገ ላለው አስደናቂ ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔርን አወደሰች።
ሉቃስ 1፥41–55