በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
የእግዚአብሔር ሙሉ የጦር ዕቃ—በመንፈሳዊነት ተጠብቆ መቆየት


ኤፌሶን 6፥11–17

የእግዚአብሔር ሙሉ የጦር ዕቃ

በመንፈሳዊነት ተጠብቆ መቆየት

ጳውሎስ በኤፌሶን ለነበሩ ቅዱሳን ከክፉው ጋር ስለምናደርገው መንፈሳዊ ውጊያ ደብዳቤ ጻፈላቸው።

ጳውሎስ በኤፊውሶን ለነበሩት ቅዱሳን ሁላችንም ከክፉው ጋር መንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ እንዳለን አስተማረ። ልክ ወታደሮች በውጊያ ወቅት አካላቸውን በጦር ዕቃ እንደሚሸፍኑ ሁሉ፣ እኛም መንፈሳችንን ለመጠበቅ መንፈሳዊ የጦር ዕቃችንን መልበስ እንችላለን።

ኤፌሶን 6፥11–13

አንዲት ወጣት ሴት የጦር እቃ ዝናር ስትታጠቅ።

የወታደርን የጦር እቃ በመንፈስ ከሚጠብቁን ነገሮች ጋር አነጻጽሮታል። ለምሳሌ፣ እውነት በወገባችን እንደምንታጠቀው ዝናር ወይም ቀበቶ ነው አለ።

ኤፌሶን 6፥14

አንድ ወጣት የደረት ጥሩር ሲታጠቅ።

በመቀጠልም፣ ጳውሎስ ጽድቅ ደረታችንን እንደሚሸፍን የደረት ጥሩር ነው አለ።

ኤፌሶን 6፥14

በጦር ዕቃ የተሸፈነ መጫሚያ እና እግር።

የኢየሱስ ክርስቶስ የሰላም ወንጌል እግራችንን እንደሚሸፍን መጫሚያ ነው።

ኤፌሶን 6፥15

አንዲት ወጣት ሴት ጋሻ ይዛ።

ልክ ጋሻ ወታደሮችን ከጠላቶቻቸው ቀስት እንደሚከላከላቸው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለን እምነት ከሰይጣን የሚከላከለን ጋሻ ነው።

ኤፌሶን 6፥16

አንድ ወጣት የራስ ቁር አድርጎ።

ጳውሎስ ደህንነት ራሳችንን እና አዕምሮአችንን እንደሚጠብቅ የራስ ቁር ነው አለ።

ኤፌሶን 6፥17

ሁለት ሰይፎች።

በመጨረሻም፣ ጳውሎስ መንፈስ እና የእግዚአብርሔር ቃል እንደሰይፍ ናቸው አለ።

ኤፌሶን 6፥17

አንዲት ሴት እና አንድ ወንድ በእግዚአብሔር ዕቃ ጦር ሙሉ ለሙሉ ተሸፍነዋል።

እያንዳንዱን የእግዚአብሔር የጦር ዕቃ በለበስን ጊዜ፣ የሰይጣንን ውሸት እና ፈተና በመቋቋም በጀግንነት መቆም እንችላለን። መንፈሳችን በደህንነት እና በብርታት አንዲጠበቁ ለመርዳት እግዚአብሔር ይህን የጦር ዕቃ ሰጥቶናል።

ኤፌሶን 6፥11–13