በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስ ሁለት ሐዋሪያትን አፅናና—በኤማሁስ ጎዳና ላይ አብሮ መጓዝ


ሉቃስ 24፥13–35

ኢየሱስ ሁለት ሐዋሪያትን አፅናና

በኤማሁስ ጎዳና ላይ አብሮ መጓዝ

ሁለቱ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ወደ ኤማሁስ ሲሄዱ።

ኢየሱስ ከሞት በተነሳበት ቀን፣ ሁለት ሐዋሪያት ከኢየሩሳሌም ኤማሁስ ወደምትባል ከተማ ይሄዱ ነበር። እነርሱ የኢየሱስ ተከታዮች ነበሩ፣ እናም አዝነው ነበር። ስለኢየሱስ ሞት እና ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የተከሰቱትን ሌሎች ነገሮች ይነጋገሩባቸው ነበር።

ሉቃስ 24፥13–14

ኢየሱስ መጣ እና ከደቀ መዛሙርት ጋር ተጓዘ። ደቀመዛሙርቱ እርሱ ኢየሱስ እንደሆነ አላወቁም ነበር።

እየተጓዙ ሳሉ፣ ኢየሱስ መጣ እናም ከእነርሱ ጋር ተጓዘ፣ ግን እነርሱ ኢየሱስ እንደነበረ አላወቁም። ስለምን እንደሚያወሩ እና ለምን እንዳዘኑ ጠየቃቸው።

ሉቃስ 24፥15–17

ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንደሞተ ገለጹ።

እርሱ ምን እንደተከሰተ ባለማወቁ ተደንቀው ነበር። ስለኢየሱስ ነገሩት። እርሱ አዳኛቸው ይሆናል ብለው አስበው ነበር፣ ግን ሞቷል።

ሉቃስ 24፥18–21

ደቀ መዛሙርቱም የኢየሱስ ሰውነት ከመቃብር ጠፍቷል አሉ።

ደግመውም አንዳንድ ሴቶች ወደ መቃብሩ ሄደው ነበር፣ ነገር ግን የኢየሱስ ሰውነት ጠፍቷል አሉ። መላእክት ለሴቶቹ ኢየሱስ ህያው እንደሆነ ነግረዋቸዋል።

ሉዋስ 24፥21–24

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሲያስተምር።

ኢየሱስ ቅዱሳት መጻህፍት ስለአዳኝ ምን እንዳሉ አስተማራቸው። ነቢያት አዳኝ ይሞታል እና እንደገና ይነሳል ብለዋል አለ።

ሉቃስ 24፥25–27

ኢየሱስ ዳቦውን ባረከ እናም ለደቀመዛሙርቱ ሰጠ።

ወደ ኤማሁስ ሲደርሱም፣ እየመሸ ነበር። ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር እንዲያድር ጋበዙት። ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ለመብላት ተቀመጠ። ዳቦን ወሰደ፣ ባረከው እና ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ። በዚያ ጊዜ፣ እነርሱ ኢየሱስ እንደሆነ አወቁ። በድንገትም ከእነርሱ ተሰወረ።

(ሉቃስ 24፥29–31)።

ደቀመዛሙርቱ ከኢየሱስ ጋር ስለነበራቸው አጋጣሚ አወሩ።

ሁለቱ ሐዋሪያት ኢየሱስ ከቅዱሳት መጻህፍት ሲያስተምራቸው እንዴት ልባቸው ይቃጠል እንደነበር ተናገሩ። ለሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ኢየሱስን እንዳዩ ለመንገር በፍጥነት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

ሉቃስ 24፥32–35