በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው—ፈተናን የመቋቋም ምሳሌ


ማቴዎስ 4፥1–10

ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው

ፈተናን የመቋቋም ምሳሌ

ኢየሱስ በምድረበዳ ሲጓዝ።

ከተጠመቀ በኋላ፣ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር ለመሆን ወደ ምድረበዳ ተጓዘ። ለ40 ቀናት ምንም አልበላም። ተልዕኮውን ለመፈጸም ይዘጋጅ ዘንድ ይጾም እና ይጸልይ ነበር።

ማቴዎስ 4፥1–2፤ በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ማስታወሻ 1b እና 2c) ተመልከቱ።

ሰይጣን ድንጋዩን ወደ ዳቦ እንዲቀይር ኢየሱስን ፈተነው።

ኢየሱስ ተርቦ ነበር። ሰይጣን መጣ እናም ፈተነው። እርሱም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ፣ ድንጋዩን ወደ ዳቦ መቀየር እንደሚችል ተናገረ። ኢየሱስም ይህን አላደረገውም። ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቃል እንጂ በዳቦ ብቻ አይኖር በማለት ቅዱሳት መጻህፍትን ጠቀሰ።

ማቴዎስ 4፥2–4

ሰይጣን ኢየሱስን ከመቅደስ ጫፍ ላይ እንዲዘል ሲፈትነው።

ከዚያም መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን ወደ መቅደስ ጫፍ አመጣው። ሰይጣን ኢየሱስን እንዲዘል ፈተነው። እርሱም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ፣ መላዕክት እንዳይጎዳ ለመጠበቅ እንደሚችሉ ተናገረ። ኢየሱስም አልዘለለም። እርሱም ለሰይጣን ቅዱሳት መጻህፍት እግዚአብሔርን መፈታተን የለብንም ብለዋል አለው።

ማቴዎስ 4፥5–7፤ በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ማስታወሻ 5a እና 6a) ተመልከቱ።

ሰይጣን ኢየሱስን እንዲሰግድለት ፈተነው።

በመቀጠልም መንፈስ ቅዱስም ኢየሱስን ወደ ተራራ ጫፍ ወሰደው። ከዚያም ላይ፣ ኢየሱስ የዓለምን መንግስታት ሁሉ ማየት ቻለ። ሰይጣንም መጥቶ ኢየሱስ ወድቆ ከሰገደለት እነዚህን መንግስታት ሁሉ እንደሚሰጠው ተናገረ።

ማቴዎስ 4፥8–10፤ በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ማስታወሻ 8a) ተመልከቱ።

ኢየሱስም ሰይጣንን እንዲሄድ ሲነግረው።

ኢየሱስም ለሰይጣን ቅዱሳት መጻህፍት እግዚአብሔር ብቻ ማምለክ እንዳለብን መናገራቸውን ነገረው። ኢየሱስም ሰይጣንን እንዲሄድ ነገረው። ኢየሱስ ወንጌሉን ለመስበክ ወደ ገሊላ ሄደ። እርሱ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ተሞልቶ ነበር።

ሉቃስ 4፥13–14