በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስ አንዲትን ሴት ፈወሰ እንዲሁም የኢያኢሮስን ሴት ልጅ ከሞት አስነሳ—”እመን ብቻ እንጂ አትፍራ”


ማርቆስ 5፥21–43

ኢየሱስ አንዲትን ሴት ፈወሰ እንዲሁም የኢያኢሮስን ሴት ልጅ ከሞት አስነሳ

“እመን ብቻ እንጂ አትፍራ”

ኢያኢሮስ ከሚስቱ እና ከሴት ልጁ ጋር።

ኢያኢሮስ የተባለ ሰው በገሊላ ባህር አጠገብ ባለች ከተማ ውስጥ ከሚስቱ እና ከሴት ልጁ ጋር ይኖር ነበር። ኢያኢሮስ አይሁድ እግዚአብሔርን በሚያመልኩበት ምኩራብ ውስጥ አለቃ ነበር።

ማርቆስ 5፥22

የኢያኢሮስ ሴት ልጅ በጣም ታምማ ነበር።

የ12 ዓመት እድሜ የነበራት የኢያኢሮስ ሴት ልጅ እጅግ ታምማ ነበር። ለሞትም ተቃርባ ነበር። ኢያኢሮስ እርዳታ እንደሚያስፈልጋት አውቋል። ኢየሱስ እነርሱ በሚኖሩበት ከተማ እንደነበርም አውቋል።

ማርቆስ 5፥22–23

ኢያኢሮስ ልጁን እንዲፈውስለት ኢየሱስን ጠየቀው።

ኢያኢሮስ ቤቱን ትቶ ሄደ እናም ኢየሱስን አገኘ። እርሱም በኢየሱስ እግር ስር ወደቀ እናም እንዲመጣ እና ልጁን እንዲፈውስለት ለመነው። ኢየሱስ ሴት ልጁን ቢባርክለት እርሷም መኖር እንደምትችል ኢያኢሮስ ያውቅ ነበር። ኢየሱስ ኢያኢሮስን ተከትሎ ወደ ቤቱ ሄደ። ብዙ ህዝብም ተከተሉት።

ማርቆስ 5፥23–24

በህዝቡም መካከል የነበረች አንዲት ሴት በኢየሱስ መፈውስን ፈለገች።

በዚሁ ከተማ የነበረች አንዲት ሴት እንዲሁ የኢየሱስን እርዳታ ፈለገች። ለ12 ዓመታት በህመም ትሰቃይ ነበር። ያላትን ሁሉ በህክምና ባለሙያዎች ላይ አባከነች፣ ነገር ግን የሚፈውሳት አልነበረም— እየባሰባት ሄደች። እርሷም ኢየሱስ ሊፈውሳት እንደሚችል አውቃ ነበር። ነገር ግን በህዝቡ መካከል አልፋ እርሱን እንዴት ልታገኘው ትችላለች?

ማርቆስ 5፥25–27

Jesus Heals Woman Raises Jairus' Daughter

ሴቲቱም የኢየሱስን የልብሱን ጫፍ ብቻ ብትነካ ልትፈወስ እንደምትችል አመነች። ኢየሱስ ሲያልፍ እሱን ለመንካት እጇን ዘረጋች። የልብሱን ጫፍ እንደነካች ወዲያውኑ ከህመሟ ተፈወሰች።

ማቴዎስ 9፥20ማርቆስ 5፥27–29ሉቃስ 8፥44

ኢየሱስ ማን እንደነካው ጠየቀ።

ወዲያውኑም ኢየሱስ መጓዙን አቆመ። ሀይል ከእርሱ እንደወጣ ተሰማው። “የዳሰሰኝ ማን ነው?” በማለት ጠየቀ። ደቀ መዛሙርቱም ግራ ገብቷቸው ነበር። ብዙ ሰዎች ነክተውታል—በህዝብ ተከብበው ነበር። ኢየሱስ ማን እንደነካው ለማወቅ ዘወር ብሎ አየ።

ማርቆስ 5፥30–32ሉቃስ 8፥45

ኢየሱስም ሴቲቱን በሰላም እንድትሄድ ነገራት።

ኢየሱስ ልብሱን የነካችው ሴት ማን እንደሆነች አየ። ስለ ህመሟ ለኢየሱስ ነገረችው፥ ኢየሱስም እንደፈወሳት ተናገረች። ኢየሱስ እንድትጽናና ነገራት። በእርሱ ባላት እምነት ምክንያት ተፈውሳለች። እርሱም “በሰላም ሂጂ፣” አላት።

ማርቆስ 5፥33–34ሉቃስ 8፥47–48

ኢያኢሮስ ሴት ልጁ እንደሞተች ተገነዘበ።

ከዚያም ከኢያኢሮስ ቤት አንድ ሰው መጣ። አሁን በጣም ዘግይቷል፤ የኢያኢሮስ ሴት ልጅ ሞታለች በማለት ተናገረ። ኢያኢሮስም ከዚህ በኋላ ኢየሱስን ሊያስጨንቀው አይገባውም።

ማርቆስ 5፥35

ኢየሱስም ለኢያኢሮስ በእርሱ እንዲያምን ነገረው።

ወዲያውኑም ኢየሱስ ይህን እንደሰማ፣ “እመን ብቻ እንጂ አትፍራ” በማለት ለኢያኢሮስ ነገረው። ከዚያም ወደ ኢያኢሮስ ቤት ሄዱ።

ማርቆስ 5፥36–38

ኢየሱስም የኢያኢሮስን ልጅ ተነሺ አላት።

ኢያኢሮስ እና ሚስቱ ልጃቸው ተኝታ ወዳለችበት ኢየሱስን መሩት። ኢየሱስም የልጅቷን እጅ በመያዝ “ተነሽ እልሻለሁ” አላት።

ማርቆስ 5፥41

የኢያኢሮስ ሴት ልጅ ዳግም ወደ ህይወት ተመለሰች።

ወዲያውኑ፣ የኢያኢሮስ ሴት ልጅ ከአልጋዋ ላይ ተነሳች። ከእንግዲህ ወዲህ ሞታ አልነበረም! ኢየሱስ ለኢያኢሮስ እና ለሚስቱ የሚበላ ነገር እንዲሰጧት ጠየቃቸው። ኢየሱስ ለልጃቸው ያደረገው ነገር አስገርሟቸዋል። ስለዚህ ተዓምር ለሌሎች ሰዎች እንዳይናገሩ ጠየቃቸው።

ማርቆስ 5፥42–43