ዮሐንስ 4
ኢየሱስ፣ አንዲት ሴት፣ እና የውሃ ጉድጓድ
ስለ ህይወት ውሃ ማስተማር
ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ ወደ ገሊላ ለመሄድ በሰማርያ አለፉ። ውሃን ለማግኘት በአንድ ጉድጓድ አጠገብ ቆሙ። ኢየሱስ በዚያ አረፍ ብሎ እያለ፣ ደቀመዛሙርት ምግብ ለመግዛት ሄዱ።
ዮሐንስ 4፥3–8
ከሰማርያ የሆነች አንዲት ሴት የውሃ ማሰሮዋን ልትሞላ ወደ ጉድጓዱ መጣች። ኢየሱስ የሚጠጣን ውሃ እንድትሰጠው ጠየቃት። ሴቲቱ ተገርማ ነበር። ኢየሱስ አይሁዳዊ ነው፣ እና አብዛኞቹ አይሁዳውያን ከሰማርያ ሰዎች ጋር አይነጋገሩም ነበር።
ዮሐንስ 4፥7–9
ኢየሱስም ከጉድጓዱ ውሃን የሚጠጡ ሰዎች ዳግም እንደሚጠሙ ነገራት። ነገር ግን እርሱ የዘለዓለም “የህይወት ውሃ” ሊሰጣት እንደሚችል እና ወደ ፊት ፈጽሞ እንደማትጠማ ነገራት። ሴቲቱም ከዚህ “የህይወት ውሃ” ጥቂት እንደምትፈልግ ነገረችው።
ዮሐንስ 4፥10–14
ኢየሱስም ሄዳ ባሏን እንድትጠራ ነገራት። እርስዋም “እኔ ባል የለኝም” አለች። ኢየሱስም አምስት ባሎች እንደነበሯት፣ እና አብሯት ይኖር የነበረው ሰው ባሏ እንዳልነበረ ነገራት።
ዮሐንስ 4፥16–18
ሴቲቱም ስለ እርሷ እነዚህን ነገሮች በማወቁ ተገረመች። እርሷም በቅርቡ አዳኝ የሆነ መምጣቱን እንደምታውቅ ተናገረች። ኢየሱስም እርሱ አዳኝ እንደሆነ ነገራት።
ዮሐንስ 4፥19፣ 25–26
ሴቲቱም የውሃ ማሰሮዋን በጉድጓዱ አጠገብ ትታ ወደ ከተማው ሄደች። ለአያሌ ሰዎችም አዳኙን እንዳገኘችው ተናገረች። እንዲመጡ እና ሲያስተምር እንዲሰሙ ጋበዘቻቸው። በዚህች ሴት ምክንያት፣ ብዙ የሰማርያ ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ።
ዮሀንስ 4፥28–29፣ 39–42