ማቴዎስ 26፥36–46፤ ሉቃስ 22፥39–46
ኢየሱስ በጌቴሴማኒ
ስለ ዓለም ኃጢአት መከራ መቀበል
ኢየሱስና ሐዋርያቱ ጌቴሴማኒ ወደምትባል የአትክልት ስፍራ ሄዱ። ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን እንዲከተሉት ጠየቃቸው፤ ሌሎቹም እንዲጠብቁ ነገራቸው።
ማቴዎስ 26፥36–37፣ ዮሐንስ 18፥1
ኢየሱስ ለጴጥሮስ፣ ለያዕቆብና ለዮሐንስ በጣም እንዳዘነ ነገራቸው። ሲጸልይ ከእርሱ ጋር ነቅተው እንዲቆዩ ጠየቃቸው።
ማቴዎስ 26፥38
ከዚያም ኢየሱስ ትንሽ ራቅ ብሎ ወደ አትክልቱ ሄደ። ንስሐ እንድንገባና ይቅር እንድንባል ስለ ኃጢአታችን መከራ መቀበል ጀመረ። ኢየሱስ እንዴት እንደሚረዳን እንዲያውቅ ህመማችን፣ ስቃያችን እና ሀዘናችን ሁሉ ተሰምቶት ነበር። ይህን ያደረገው ስለወደደን ነው። ይህ ሁሉ የሰማይ አባት ዕቅድ አካል ነበር።
ማቴዎስ 26፥39፤ ሉቃስ 22፥41፤ ሮሜ 3፥23፤ አልማ 7፥11–13፤ 3 ኔፊ 27፥19።
ኢየሱስ የደረሰበት ሥቃይ በጣም አሳዛኝ ከመሆኑ የተነሳ የሰማዩ አባት ስቃዩን ማስወገድ ይችል እንደሆነ ጠየቀው። ነገር ግን አባቱ እንዲያደርገው የሚፈልገውን ለማድረግ ፈቃደኛ ነበር። እርሱም “የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ” አለ።
ሉቃስ 22፥42
ኢየሱስም ወደ ጴጥሮስ፣ ወደ ያዕቆብና ወደ ዮሐንስ ሲመለስ ተኝተው እንደነበሩ አየ። ከእንቅልፉቸው አስነሳቸው እንዲሁም ነቅተው እንዲጸልዩ በድጋሚ ጠየቃቸው። ነገር ግን ነቅተው ለመቆየት ቢፈልጉም በጣም እንደደከሙ ያውቅ ነበር።
ማቴዎስ 26፥40–41
ኢየሱስ እንደገና ጸለየ። አንድ መልአክ ማበረታቻ ሊሰጠው መጣ። በጣም ስቃይ ተሰምቶት ነበር፣ እናም የበለጠ ጸለየ። ላቡ መሬት ላይ የሚወድቅ የደም ጠብታዎች ነበሩ።
ማቴዎስ 26፥42፤ ሉቃስ 22፥43–44፤ ሞዛያ 3፥7፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥16–19
ኢየሱስ በተጨማሪ ሁለት ጊዜ ወደ ጴጥሮስ፣ ወደ ያዕቆብና ወደ ዮሐንስ ሄዶ ተኝተው አገኛቸው። በመጨረሻም ቀሰቀሳቸው፣ ምክንያቱም የሚወሰድበት ጊዜ ደርሱ ነበርና።
ማቴዎስ 26፥43–46