በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
በክርስቶስ ሁሉም ሕያዋን ይሆናሉ—ጳውሎስ ስለትንሳኤ አስተማረ


1 ቆሮንቶስ 15

በክርስቶስ ሁሉም ህያዋን ይሆናሉ

ጳውሎስ ስለትንሳኤ አስተማረ

ጳውሎስ በቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን ለነበሩ ሰዎች ደብዳቤ እየጻፈ። ሁሉም አንዲት በሞተች ሴት አጠገብ ተሰብስበዋል።

ቆሮንቶስ በተባለች ከተማ ባለች ቤተክርስቲያን የነበሩ አንዳንድ አባላት ከሞትን በኋላ ስለሚሆነው ነገር ጥያቄ ነበራቸው። ኢየሱስ ከሞት ስለመነሳቱ እርግጠኞች አልነበሩም። አንዳንድ ሰዎች ትንሳኤ የለም ይላሉ። ጳውሎስ ይህንን ሰማና በቆሮንቶስ ለነበሩ ቅዱሳን ደብዳቤ ጻፈላቸው።

1 ቆሮንቶስ 15፥12–14

ከሞት የተነሳው ኢየሱስ ከደቀመዛሙርት ጋር ሲነጋገር።

ጳውሎስ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ የወንጌሉ አስፈላጊው ክፍል እንደሆነ ተናገረ። ጳውሎስም “ክርስቶስ ስለሃጢያታችን ሞተ፣” እንዲሁም “በሶስተኛውም ቀን ዳግም ከሞት ተነሳ” አለ። ከትንሳኤው በኋላ ጳውሎስን እና ሌሎች ደቀ መዛሙርትን ጨምሮ ከ500 በላይ የሚሆኑ ሰዎች አይተውታል።

1 ቆሮንቶስ 15፥1–8

ጳውሎስ ደብዳቤ እየጻፈ፤ አዳም እና ሄዋን የኤደን ገነትን ትተው ሲሄዱ፤ እና ኢየሱስ በመቃብር አጠገብ ቆሞ።

ጳውሎስ ክርስቶስ ከሞት ያልተነሳ ከሆነማ፣ ሁላችንም ሃዘንተኛ እና ተስፋ የሌለን እንደምንሆን አስተማረ። በአዳም ውድቀት ምክንያት ሁላችንም እንሞታለን፣ ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ሁላችንም በትንሳኤ እንነሳለን።

1 ቆሮንቶስ 15፥17–22

አንዲት ሴት እየተጠመቀች።

ሰዎች ለሞቱ ሰዎች እየተጠመቁ እንደሆነ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ቅዱሳን አስታወሳቸው። የሞቱ ሰዎች በጭራሽ የማይነሱ ከሆነ ያንን ማድረግ ለምን ያስፈልገናል? እያንዳንዱ ሰው ከሞት እንደሚነሳ ስለምናውቅ ለሙታን እንጠመቃለን። ይህ የጌታን በረከት ይቀበሉ ዘንድ እድልን ይሰጣቸዋል።

1 ቆሮንቶስ 15፥29

አንዲት ሴት በኢየሱስ አጠገብ ተንበርክካ።

በቆሮንቶስ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች ከሞት ስንነሳ ሰውነታችን ምን ሊመስል እንደሚችል ግራ ተጋብተው ነበር። ጳውሎስ ሰውነታችን የከበረ አንደሚሆን ተናገረ። አይደክሙም ወይም አይታመሙም ወይም አያረጁም። አንዳንድ ሰዎች እንደጸሃይ የደመቀ የሰለስቲያል አካል ይኖራቸዋል። አንዳንዶቹ እንደጨረቃ ይደምቃሉ፣ ሌሎች ደግሞ እንደከዋክብት የደመቁ ይሆናሉ።

1 ቆሮንቶስ 15፥35፣ 40–43ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥96–9888፥20–23