የሐዋርያት ስራ 9፥1–31
ኢየሱስ ለሳኦል ተገለጠ
ንስሐ ለመግባት እና ጌታን ለመከተል የቀረበ ግብዣ
ሳኦል ፈሪሳዊ ነበር—ቅዱሳት መጻሕፍትን ጠንቅቆ የሚያውቅ የአይሁድ መሪ። ሳኦል ግን ኢየሱስ አዳኝ ነው ብሎ አያምነም ነበር። ብዙ ጊዜ የኢየሱስን ተከታዮች ወደ እስር ቤት አስገቡቷቸዋል። ከዕለታት አንድ ቀን ሳኦል የኢየሱስን ተከታዮች በቁጥጥር ስር አውሎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመውስድ ወደ ደማስቆ ወደምትባል ከተማ ሄዴ።
የሐዋርያት ስራ 9፥1–2፤ 22፥4–5፤ 26፥5
ሳኦልም ሲጓዝ ድንገት ብርሃን በራበት። ከፀሐይ የበለጠ ብሩህ ነበር። ሳኦልም መሬት ላይ ወደቀ። “ሳኦል፣ ሳኦል” የሚል ድምፅ ሰማ። ድምፁም ሳኦልን ከኢየሱስ ጋር ለምን እንደሚዋጋ እና ደቀ መዛሙርቱን እንደሚጎዳ ጠየቀው።
የሐዋሪያት ሥራ 9፥3–4፤ 26፥13–14
ሳኦልም ማን እየተናገረ እንደሆነ ጠየቀ። ድምፁም “እኔ ኢየሱስ ነኝ” አለው። ሳኦልም ፈራ እናም ተገረመ። ኢየሱስን ምን ማድረግ እንዳለበት ጠየቀው። ኢየሱስም ሳኦልን፣ “ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባ” አለው። እዚያም ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለበት ይማራል።
የሐዋርያት ስራ 9፥5–6
ሳኦልም ታዘዘ እናም ተነሣ። አሁን ግን ዓይነ ስውር ነበር። ምንም ነገር ማየት አልቻለም። አብረውት የሄዱት ሰዎች ወደ ደማስቆ ከተማ ወሰዱት። ሳኦልም ለሦስት ቀን ምንም አልበላም ወይም አልጠጣም።
የሐዋርያት ስራ 9፥8–9
በደማስቆ ይኖሩ ከነበሩት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አንዱ ሐናንያ ነበር። ኢየሱስም ሐናንያን በራእይ ጎበኘውና ሄዶ ሳኦልን እንዲረዳው ነገረው።
የሐዋርያት ስራ 9፥10–12
ሐናንያ ግን ግራ ተጋብቶ ነበር። ስለ ሳኦል ሰምቶ ነበር። ሳኦል ከኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ጋር ምን ያህል እንደተዋጋ ያውቅ ነበር።
የሐዋርያት ስራ 9፥13–14
ኢየሱስ ሐናንያ ሳኦልን ምንም ቢሆን እንዲረዳው ጠየቀው። ኢየሱስ ሳኦልን የመረጠው አይሁድ ላልሆኑ እና ስለ እርሱ ለማያውቁ ብዙ ሰዎች ወንጌሉን እንዲወስድ ነው አለ።
የሐዋርያት ስራ 9፥15–16
ሐናንያ ኢየሱስን ታዘዘ። ሳኦልም አግኝቶ በረከት ሰጠው። ሐናንያም “ወንድም ሳኦል” ብሎ ጠራው።
የሐዋርያት ስራ 9፥17
ሐናንያ ኢየሱስ የላከው ሳኦል እንዲፈወስና በመንፈስ ቅዱስ እንዲሞላ ነው አለ። ወዲያውኑም ሳኦል እንደገና ማየት ቻለ።
የሐዋርያት ስራ 9፥17–18
ሳኦልም ተጠመቀ። ከዚያም በከተማው ውስጥ ያሉትን ሁሉ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተማረ። ሕዝቡም ሳኦል በጣም ስለተለወጠ ተገረሙ። በቀሪው የሕይወት ዘመኑ ሳኦል ጳውሎስ ተብሎ ይጠራ ነበር። አይሁዶችንና ሌሎችንም ሁሉ በኢየሱስ እንዲያምኑ አስተማረ። ጳውሎስ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ሆነ።
የሐዋሪያት ሥራ 9፥18–22፣ 29–31፤ 13፥9