ዮሐንስ 5፥1–17
ኢየሱስ በቤተ ሳይዳ መጠመቂያ
ለረዥም ጊዜ ታሞ የነበረውን ሰው መፈወስ
በኢየሩሳሌም፣ የቤተ ሳይዳ መጠመቂያ የሚባል ስፍራ ነበር። ይህ መጠመቂያ የመፈወስ ሃይል እንዳለው ሰዎች ያምኑ ነበር። ህመምተኞች፣ አይነ ስውራን፣ ወይም መራመድ የማይችሉ አያሌ ሰዎች ወደዚህ ስፍራ ይመጡ ነበር።
ዮሐንስ 5፥2–3
በሆነ ጊዜ፣ መልአክ መጥቶ የመጠመቂያውን ውሃ እንደሚያናውጠው ሰዎች ያምኑ ነበር። ውሃው ሲናወጥ የሚገባው የመጀመሪያው ሰው ከያዘው ከማንኛውም ህመም ይፈወስ ነበር። ብዙ ሰዎች በመጠመቂያው ውስጥ በመጀመሪያ ለመግባት ይሞክሩ ነበር።
ዮሐንስ 5፥4
በመጠመቂያው አካባቢ ከነበሩት መሃል መራመድ የማይችል አንድ ሰው ነበር። ለ38 ዓመታት የታመመ ነበር። ይፈወስ ዘንድ ወደ ውሃው ሊገባ ፈለገ፣ ነገር ግን በሞከረ ጊዜ ሁሉ ሌላ ሰው ይቀድመው ነበር።
ዮሐንስ 5፥5–7
በአንድ የሰንበት ቀን፣ ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ነበር። በከተማውም አልፎ ሲሄድ፣ ወደ ቤተ ሳይዳ መጠመቂያ መጣ እናም በዚያ ተኝቶ የነበረን አንድ ሰው አየ።
ዮሐንስ 5፥6
ይህም ሰው ለረዥም ጊዜ ይታመም እንደነበር እና መራመድም እንደማይችል አውቆ ነበር። ኢየሱስም ሰውየው ይፈወስ ዘንድ እንደሚፈልግ ጠየቀው።
ዮሐንስ 5፥6
ሰውየውም ወደ መጠመቂያው እንዲገባው የሚረዳው ማንም ሰው በዚያ እንዳልነበረ እና ውሃውም ሲናወጥ ሌሎች ቀድመውት እንደሚገቡ ለኢየሱስ ነገረው።
ዮሐንስ 5፥7
ኢየሱስም ለሰውየው “ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” አለው። ወዲያውኑም ሰውየው ተፈወሰ። ከዚያም ተነስቶ አልጋውን ተሸከመ። ከ38 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መራመድ ቻለ!
ዮሐንስ 5፥8–9
የአይሁድ መሪዎች ሰውየው አልጋውን ተሸክሞ ሲሄድ አዩት። አልጋውን ተሸክሞ በመሄዱ ስራ የሰራ መስሎ ስለታያቸው የሰንበትን ቀን እያከበረ አይደለም አሉ። ሰውየውም ገና እንደተፈውሰ፣ እና የፈወሰውም ሰው አልጋህን ተሸክመህ ሂድ እንዳለው ገለጸላቸው።
ዮሐንስ 5፥10–11
ሰውየውን በሰንበት የፈወሰው እና አልጋውንም ተሸክሞ እንዲሄድ ያዘዘው ኢየሱስ እንደነበር መሪዎች አወቁ። እነርሱም በኢየሱስ ተቆጡ እናም እርሱን ለመግደል ፈለጉ። ኢየሱስም የሰማይ አባቱ እንዲያደርግ ያዘዘውን ነገሮች ብቻ እያደረገ እንደሆነ ነገራቸው።
ዮሐንስ 5፥15–17