ማቴዎስ 27፤ ሉቃስ 23፤ ዮሐንስ 19
ኢየሱስ ሕይወቱን ለእኛ አሳልፎ ሰጠ
ከኃጢአት እና ከሞት ለማዳን መስዋዕት ሆነ
ጲላጦስ ኢየሱስ እንዲሰቀል ከወሰነ በኋላ ለወታደሮቹ ኢየሱስን እንዲወስዱት ነገራቸው። እነርሱም እርሱን ገረፉት፣ ተፉበት፣ በራሱም ላይ የእሾህ አክሊል ደፉበት፣ እንዲሁም አፌዙበትም።
ማርቆስ 15፥15–20
ወታደሮቹ ኢየሱስ ከባድ የእንጨት መስቀል እንዲሸከም አደረጉት። ከኢየሩሳሌም ውጭ ወደምትገኘው ጎልጎታ ወደምትባል ስፍራ ወሰዱት።
ዮሐንስ 19፥17
ወታደሮቹ የኢየሱስን እጆችና እግሮች በመስቀል ላይ ቸነከሩ። ኢየሱስ የሰማይ አባቱ ወታደሮቹን ይቅር እንዲላቸው ጠየቀ፣ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ልጅ እየሰቀሉ እንደሆነ ስለማያውቁ።
ሉቃስ 23፥33–34፤ በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ 34c ተመልከቱ።
በዚያን ቀን ሁለት ወንጀለኞች ከኢየሱስ ጋር ተሰቅለው ነበር። ከእነርሱም አንዱ፣ “አንተስ ክርስቶስ አይደለህምን? ራስህንም እኛንም አድን” አለው።
ሉቃስ 23፥39
ሌላው ወንጀለኛም ለእነርሱ ቅጣታቸው ይገባቸዋል፣ ኢየሱስ ግን ምንም ጥፋት አልሠራም አለ። ኢየሱስንም በመንግሥቱ እንዲያስበው ጠየቀው። ኢየሱስ በቅርቡ በመንፈስ ዓለም አብረው እንደሚሆኑ ነገረው።
ሉቃስ 23፥40–43
ኢየሱስ ክርስቶስን የተከተሉ ብዙ ሴቶች ከእርሱ ጋር ለመሆን ወደ መስቀል መጥተው ነበር። ከሴቶቹ አንዷ የኢየሱስ እናት ማርያም ነበረች። ኢየሱስም እርሷን አየ እናም ከሐዋርያቱ አንዱ የሆነውን ዮሐንስ እንዲንከባከባት ነገረው።
ዮሀንስ 19፥25–27፤ ደግሞም ሉቃስ 8፥1–3፤ ማርቆስ 15፥40–41 ተመልከቱ።
ለሦስት ሰዓታት ያህል ጨለማ ምድሪቱን ሸፈነ። ኢየሱስ በጣም ብቸኝነት ተሰማው። የሰማይ አባቱ እንደተወው ተሰማው።
ማቴዎስ 27፥45–46
በመጨረሻም ኢየሱስ መከራውን እንደጨረሰ አወቀ። እርሱም፣ “አባት ሆይ፤ ተፈጸመ፤ ፈቃድህም ተፈጸመ” አለ። ከዚያም ኢየሱስ አንገቱን ደፍቶ ሕይወቱን አሳልፎ ሰጠ። በእውነት መሞቱን ለማየት አንድ ወታደር ጎኑን በጦር ወጋው።
የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ማቴዎስ 27፥54 (በማቴዎስ 27፥50፣ የግርጌ ማስታወሻ a)፤ ዮሐንስ 19፥28–30፣ 34 ተመልከቱ።
ኢየሱስ ሲሞት፣ ምድርም ተናወጠች። ዓለቶችም ተሰነጠቁ። የቤተመቅደሱ መጋረጃ፣ በቤተመቅደሱ ውስጥ የተቀደሰውን ቦታ የሚሸፍነው መጋረጃ፣ ለሁለት ተቀደደ።
ማቴዎስ 27፥51
ወታደሮቹ ፈሩ። እነርሱም፣ “ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበር” አሉ።
ማቴዎስ 27፥54
የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አስከሬኑን በጨርቅ ጠቅልለው በአትክልት ስፍራ ውስጥ ባለው መቃብር ውስጥ አስቀመጡት። በኋላም በመቃብሩ በር ፊት ለፊት አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባለሉ።
ማቴዎስ 27፥57–61፤ ዮሐንስ 19፥38–41