1 እና 2 ጢሞቴዎስ
ለጢሞቴዎስ የተላኩ ደብዳቤዎች
ጳውሎስ ወጣት ጓደኛውን ይመክራል
ጢሞቴዎስ በኢየሱስ ክርስቶስን ብርቱ ዕምነት የነበረው ወጣት ነበር። እናቱ ኤውንቄ እና ሴት አያቱ ሎይድ ታላቅ እምነት የነበራቸው ሴቶች ነበሩ። ጢሞቴዎስ ገና ትንሽ ልጅ እያለ ከቅዱሳት መጻህፍት አስተምረውት ነበር ።
2 ጢሞቴዎስ 1፥5፤ 3፥15
ጢሞቴዎስ እና ጳውሎስ ጥሩ ጓደኛሞች ነበሩ። ጌታን በማገልገል እና ወንጌልን በማካፈል አብረው ሰርተዋል፣ አብረውም ተጉዘዋል። ጳውሎስ ጢሞቴዎስን እንደልጅ ይወደው ነበር።
ፊሊጲስዩስ 2፥19–22፤ 1 ጢሞቴዎስ 1፥2
ጢሞቴዎስ በኤፌሶን የሚገኘውን ቤተክርስቲያን እንዲመራ ጳውሎስ ጠየቀው። ጳውሎስ ወደ ሌላ ከተማ መሄድ ነበረበት፡፡ ሄዶም ሳለ፣ ጢሞቴዎስን ለመርዳት ደብዳቤ ይጽፍለት ነበር።
1 ጢማቴዎስ 1፥1–3
በኋላም፣ ጳውሎስ በሮሜ እስር ቤት በነበረበት ጊዜ፣ ለጢሞቴዎስ ሌላ ደብዳቤ ጻፈለት። ከባድ ጊዜ እንደሚመጣ ጢሞቴዎስን አስጠነቀቀ። አንዳንድ ሰዎች ከእውነት የሚያፈገፍጉ እና ከእግዚአብሔር ይልቅ የአለምን ነገሮች የሚወዱ ይሆናሉ። እውነት ያልሆኑ ነገሮችን ያስተምራሉ።
2 ጢማቴዎስ 3፥1–7፣ 4፥3–4
ጳውሎስም ጢሞቴዎስ እንዳይፈራ ነገረው። “እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም” አለው። ጳውሎስም ጢሞቴዎስ የተማራቸውን ነገሮች ማድረግ እንዲቀጥል ነገረው። ቅዱሳት መጻሕፍት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመሩታል።
2 ጢማቴዎስ 1፥7–9፣ 3፥14–17
ጳውሎስ ህይወቱ በቅርቡ እንደሚያበቃ ታውቆት ነበር። ነገር ግን መሞትን አልፈራም። ጳውሎስ ምንም እንኳ ብዙ ተግዳሮቶች በህይወቱ ቢገጥሙትም፣ እምነቱን አጠንክሮ እንደያዘ ለጢሞቴዎስ ነገረው። የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ የዘለአለምን ህይወት እንደሚሰጡት ያምን ነበር።
2ኛ ጢማቴዎስ 4፥6–8