2 ቆሮንቶስ 12፥7–10
ኢየሱስ ደካማ ነገሮችን ጠንክራ ሊያደርግ ይችላል
በ“እሾህ”ላይ የተመሰረተ የጳውሎስ ትምህርት
ሐዋርያው ጳውሎስ ታላቅ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ነበር። እርሱ ብዙ ራዕዮች ነበሩት እንዲሁም ሰዎችን ስለ አዳኙ ያስተምር ነበር። ነገር ግን ጳውሎስ ብዙ ተግዳሮቶችም ነበሩበት።
2 ቆሮንቶስ 12፥7
ለቤተክርስቲያኗ አባላት በጻፈው ደብዳቤ ውስጥ፣ ጳውሎስ የነበረበትን ተግዳሮት በቆዳው ላይ ተጣብቆ ከነበረ እሾህ ጋር አነጻጽሮታል። ይህም ጳውሎስ እጅግ ደካማ እንደሆነ እንዲሰማው አድርጎታል።
2 ቆሮንቶስ 12፥7
ጳውሎስ ጌታ ፈተናዎቹን ከላዩ ላይ እንዲያነሳለት ሶስት ጊዜ በጸሎት ጠየቀ። ነገር ግን ጌታ አላነሳለትም።
2 ቆሮንቶስ 12፥8–9
ይልቁኑም፣ ጌታ ጳውሎስን ጠንካራ ሊያደርገው የሚችል በቂ ሃይል እንዳለው ነገረው። አንዳንድ ጊዜ ወደጌታ ከተመለስን እና እርዳታውን የምንጠይቅ ከሆነ ተግዳሮቶች መልካም እንደሆኑ ጳውሎስ ተማረ። ደካማ የመሆን ስሜት ሲሰማን፣ ምንም እንኳ ተግዳሮቶቻችን የማይሄዱ ቢሆን ኢየሱስ ጠንካራ ሊያደርገን ይችላል።
2 ቆሮንቶስ 12፥9–10