የሐዋርያት ስራ 12፥1–17
መልአክ ጴጥሮስን ከእስር ቤት አወጣው
እግዚአብሔር ጸሎቶችን ይመልሳል
ሄሮድስ የተባለ ንጉሥ ክርስቲያኖችን አይወድም ነበር። ሐዋርያው ያዕቆብን ገደለው። ከዚያም ጴጥሮስን ወደ እስር ቤት አስገባው። እስር ቤቱን እንዲጠብቁ 16 ወታደሮችን አስቀመጠ።
የሐዋርያት ስራ 12፥1–4
የቤተክርስቲያኗ አባላት ይህን በሰሙ ጊዜ ስለ ጴጥሮስ ወደ ሰማይ አባት ጸለዩ።
የሐዋሪያት ስራ 12፥5
አንድ ምሽት፣ ጴጥሮስ ተኝቶ ነበር። በሁለት ወታደሮች መካከል በሁለት ሰንሰለት ታስሮ ነበር።
የሐዋሪያት ስራ 12፥6
ድንገት በእስር ቤቱ ውስጥ ብርሃን በራ እንዲሁም አንድ መልአክ ታየ። መልአኩም “ፈጥነህ ተነስ” አለን እናም ሰንሰለቶቹም ከጴጥሮስ እጅ ወደቁ። መልአኩም ጴጥሮስን እንዲከተለው ነገረው።
የሐዋርያት ስራ 12፥7–8
ጴጥሮስም እያለመ እንደሆነ አሰበ። መልአኩን በመከተል ዘበኞቹን አልፎ ሄደ። ወደ ከተማይቱ የሚወስደው የብረት በር በራሱ ተከፈተ፤ ጴጥሮስና መልአኩም በእርሱ ውስጥ አለፉ።
የሐዋርያት ስራ 12፥9–10
መልአኩ ሄደ፤ ጴጥሮስም እያለመ እንዳልሆነ ተገነዘበ። ጌታ ሊያድነው መልአኩን እንደላከ አወቀ።
የሐዋርያት ስራ 17፥10–11
ጴጥሮስ ማርያም ወደምትባል አንዲት ሴት ቤት ሄደ፤ በዚያም ብዙ የቤተክርስቲያን አባላት ለመጸለይ መጥተው ነበር። በሩን አንኳኳ።
የሐዋርያት ስራ 12፥22–13
ሮዴ የተባለች ሴት ወደ በሩ መጣች። የጴጥሮስን ድምፅ ስትሰማ በጣም ተደሰተች! ለሌሎቹ ለመንገር ሮጠች።
የሐዋርያት ስራ 12፥13–14
ሮዴ ጴጥሮስ በሩ ላይ እንዳለ ለሁሉም ስትነግራት አላመኗትም። ጴጥሮስ ማንኳኳቱን ቀጠለ።
የሐዋርያት ስራ 12፥15–16
በመጨረሻም በሩን ከፍተው እውነት መሆኑን አዩ። ጴጥሮስ ደህና ነበር! ጌታ ጸሎታቸውን መለሰላቸው። ጴጥሮስም ጌታ ከእስር ቤት እንዴት እንዳወጣው ለሁሉም ተናገረ።
የሐዋርያት ስራ 12፥16–17