በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
“ለእኔ አደረጋችሁት”—ሌሎችን ስናገለግል፣ ኢየሱስን እያገለገልን ነን


ማቴዎስ 25፥31–46

“ለእኔ አደረጋችሁት”

ሌሎችን ስናገለግል፣ ኢየሱስን እያገለገልን ነን

ኢየሱስ ወደ ምድር ሲመለስ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ወደአባቱ ከተመለሰ በኋላ፣ ወደምድር ከሁሉም ቅዱስ መላእክት ጋር ተመልሶ እንደሚመጣ ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው። አንድ ቀን፣ ከሁሉም ሀገራት የመጡ ህዝብ በፊቱ ይሰበሰባሉ—የተከተሉትም ሆነ ያልተከተሉት ህዝብ።

ማቴዎስ 25፥31–33

አንድ ሰው ለሌላ ሰው ምግብ ሲሰጠው።

ኢየሱስ የሚከተሉትን ህዝብ በተራበበት ጊዜ ስለመገቡት ወደ መንግስቱ መግባት እንደሚችሉ ነገራቸው። ሲጠማው፣ የሚጠጣውን ሰጥተውት ነበር።

ማቴዎስ 25፥34–35

አንድ ሴት የታመመችን ሌላ ሴት ስትጎበኝ።

በሚያስፈልገውም ጊዜ ልብስ እናም የሚቆይበት ቦታ ሰጡት። ሲታመም ወይም ሲታሰር፣ እርሱን ጎበኙት።

ማቴዎስ 25፥36

ኢየሱስ እርስ በርስ እንዴት እንደምንዋደድና እርሱንም እንዴት እንደምንወድ ሲያስተምር።

ህዝቡም ኢየሱስን እነዚህን አይነት ደግ ነገሮች መቼ እንዳደረጉለት ይጠይቁታል። አዳኙም ለሌሎች ሰዎች መልካም ነገር ስናደርግ፣ መልካም ነገርን ለእርሱ እያደረግን እንደሆነ ያስረዳል።

ማቴዎስ 25፥37–40

አንድ ሴት እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ምግል ለመስጠት እምቢ አለች።

ኢየሱስ ላልተከተሉት ህዝቦች መንግስቱ ውስጥ መግባት እንደማይችሉ ይናገራል። ሲርበው እና ሲጥመው ምግብም ሆነ መጠጥ አልሰጡትም።

ማቴዎስ 25፥41–42

እርዳታ የሚያስፈልገው ሰው ብቻውን ተቀምጦ።

ልብስ ወይም የሚቆይበት ቦታ ሲያስፈልገው እነርሱ አልረዱትም። ሲታመም ወይም ሲታሰር፣ እርሱን አልጎበኙትም።

ማቴዎስ 25፥43

ኢየሱስ እርስ በርስ እንዴት እንደምንዋደድና እርሱንም እንዴት እንደምንወድ ማስተምሩን ቀጠለ።

ኢየሱስም እርዳታ የሚያስፈልገውን ለመርዳት ስንመርጥ፣ እርሱን ለመርዳት እንዳልመረጥን ገለጽ። ሌሎችን ለመርዳት ስንመርጥ፣ ኢየሱስን ለመርዳት እየመረጥን ነን።

ማቴዎስ 25፥45