በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስ ሐዋሪያቱ በጎቹን እንዲመግቡ ጠየቀ—ሌሎችን ስለእርሱ በማስተማር ለኢየሱስ ፍቅርን ማሳየት


ዮሀንስ 21ማቴዎስ 28፥16–20ማርቆስ 16፥15–19

ኢየሱስ ሐዋሪያቱ በጎቹን እንዲመግቡ ጠየቀ

ሌሎችን ስለእርሱ በማስተማር ለኢየሱስ ፍቅርን ማሳየት

ጴጥሮስ እና ሌሎች ሐዋሪያት አሳ ለማጥመድ ሄዱ።

ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ፣ ጴጥሮስ እና አንዳንድ ሌሎች ሐዋሪያት አሳ ለማጥመድ ሄዱ። ምንም እንኳን ምሽቱን በሙሉ አሳ ቢያጠምዱም፣ ምንም አላገኙም።

ዮሀንስ 21፥1–3

ኢየሱስ ሐዋሪያትን አሳ እንዳጠመዱ ጠየቃቸው።

በሚቀጥለው ቀን ጠዋት፣ ሐዋሪያቱ ኢየሱስን በባህር ዳር ላይ አዩት፣ ነገር ግን እርሱ እንደሆነ አላወቁም። አሳ እንዳጠመዱ ጠየቃቸው። አላጠመድንም አሉት።

ዮሀንስ 21፥4–5

ሐዋሪያት በአሳ የተሞላን መረብ ወደ ታንኳው ለማስገባት ሲጎትቱ።

ኢየሱስም ሐዋሪያት መረቡን በታንኳይቱ በስተቀኝ እንዲጥሉት እና አሳ እንደሚያገኙ ነገራቸው። ሐዋሪያት ኢየሱስ እንዳለው አደረጉ፣ እና፣ ከአንድ መቶ በላይ አሳዎች መረቡን ሞሉ። መረቡ በአሳ ተሞልቶ ከባድ ስለነበር ሐዋሪያቱ ወደ መርከቡ ጎትተው ሊያስገቡት አልቻሉም።

ዮሀንስ 21፥6

ጴጥሮስ ወደ ኢየሱስ ለመሄድ ሲዋኛ።

ከዚያም ዮሀንስ ሰውየው ማን እንደሆነ አወቀ። ለጴጥሮስም “ጌታ እኮ ነው” አለው። ጴጥሮስ ወደ ባህሩ ዘለለ እናም ወደ ኢየሱስ ዋኘ። ሌሎቹ ሐዋሪያት መርከቡን እና አሳዎቹን ወደ ባህር ዳር አመጡት። ኢየሱስ ዳቦ እና አሳ እየጠበሰ ነበር፣ እንዲሁም ሐዋሪያት ከእርሱ ጋር እንዲበሉ ጋበዛቸው።

የዮሀንስ ወንጌል 21፥7–13

ኢየሱስ ጴጥሮስ ጠቦቶቹን እንዲመግብ ነገረው።

ከበሉ በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስን “ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?” አለው። ጴጥሮስም አዎን አለ። ከዚያም ኢየሱስ “ግልገሎቼን አሰማራ”

ዮሐንስ 21፥15

ጴጥሮስም ለኢየሱስ እወድሀለሁ አለው።

ከዚይም ኢየሱስ ጴጥሮስን ትወደኛለህ ብሎ ጠየቀው። እንደገናም፣ ጴጥሮስ አዎን አለ። ኢየሱስም “ጠቦቶቼን ጠብቅ” አለው

ዮሀንስ 21፥16

ኢየሱስ እርሱን የሚከተሉትን ሰዎች እንዲንከባከብ ጴጥሮስን አስተማረው።

ኢየሱስ ጴጥሮስን ለሶስተኛ ጊዜ ትወደኛለህ ብሎ ጠየቀው። ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም እንደገና “በጎቼን አሰማራ” አለው። ጴጥሮስ እርሱን የሚከተሉትን ሰዎች እንዲንከባከብ ፈልጎ ነበር።

ዮሀንስ 21፥17

ኢየሱስ ሐዋሪያት ወንጌልን እንዲካፈሉ ነገራቸው።

በኋላም፣ ኢየሱስ ሐዋሪያቱ ከእርሱ ጋር በተራራ ላይ እንዲገናኙ ጠየቃቸው። በዚያም ወንጌሉን ለአለም ሁሉ እንዲካፈሉ፣ ለሰዎች ትእዛዛቱን እንዲያስተምሩ፣ እና የሚያምኑትን ሁሉ እንዲያጠምቁ ነገራቸው። “ምስክሮቼ ትሆናላችሁ” አላቸው። ከእነርሱ ጋር እንደሚገኝ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ በኩል ሀይል እንደሚሰጣቸው ቃል ገባላቸው።

ማቴዎስ 28፥16–20ማርቆስ 16፥15–19የሐዋሪያት ስራ 1፥8

ኢየሱስ ወደ ሰማይ አረገ።

ከዚያም ኢየሱስ ወደ ሰማይ በዳመና ላይ አረገ። ወደ ሰማይ አባቱ ተመለሰ። ሐዋሪያት እርሱ ሲሄድ እየተመለከቱ ሳሉ፣ ሁለት መላእክት መጡ። ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሄዷል፣ አንድ ቀን በዚህ መንገድ ወደ ምድር እንደገና ይመለሳል አሏቸው።

የሐዋሪያት ስራ 1፥9–11