ማርቆስ 14–15፤ ሉቃስ 22–23፤ ዮሀንስ 18–19
ኢየሱስ ታሰረ
የእግዚአብሔር ልጅ ላይ መፍረድ
ኢየሱስ በጌቴሴማኒ መፀለዩን እና መሰቃየቱን ከፈፀመ በኋላ፣ ይሁዳ ከብዙ የአይሁድ ጠባቂዎች ጋር መጣ። ይሁዳ ከሐዋሪያቱ አንዱ ነበር። ኢየሱስ በየጊዜው ወደዚህ የአትክልት ስፍራ ይሄድ እንደነበር ያውቃል። የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን አግኝተው እንዲወስዱት እንዲረዳቸው ይሁዳን ከፍለውት ነበር።
ዮሀንስ 18፥2–3
ጠባቂዎቹ ኢየሱስን ለመውሰድ በሚሞክሩበት ግዜ፣ ጴጥሮስ ሰይፍን መዘዘ። የሊቀካህንን አገልጋይ ጆሮ ቆረጠው።
ዮሀንስ 18፥10
ኢየሱስ ጴጥሮስ ሰይፉን እንዲያስቀምጠው ነገረው። ኢየሱስም አባቱ የሚፈልገውን ማድረግ አለብኝ አለ።
ዮሀንስ 18፥11
ኢየሱስ የአገልጋዩን ጆሮ ነካ እና ፈወሰው።
ሉቃስ 22፥51
ጠባቂዎቹ ኢየሱስን ወደ ሊቀ ካህኑ ቤት ወሰዱት። ሌሎች የአይሁድ መሪዎችም በዚያ ነበሩ። ኢየሱስን ለማስገደል ምክኛት ይፈልጉ ነበር። ስለእርሱ ውሸት የሚናገር ሰዎችን አመጡ።
ማርቆስ 14፥53–61
በመጨረሻም፣ ሊቀ ካህኑም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ጠየቀው። ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “እኔ ነኝ።”
ማርቆስ 14፥61–62
ይህም ሊቀ ካህኑን እና ሌሎች መሪዎችን እንዲናደዱ አደረገ። ኢየሱስን መቱት፣ ተፉበት እናም አፌዙበት። እርሱ መገደል እንዳለበት ተስማሙ።
ማርቆስ 14፥63–65
ኢየሱስ በሊቀ ካህኑ ቤት ውስጥ ሳለ፣ ጴጥሮስ በውጪ ነበር። በእሳት አጠገብ ለመሞቅ ተቀመጠ። ለሶስት ጊዜ፣ ሰዎች ጴጥሮስን ከኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አንዱ መሆኑን እንዳወቁ አመለከቱ። ነገር ግን በእያንዳንዱ ጊዜ፣ ጴጥሮስ ኢየሱስን አላውቅም አለ።
ማርቆስ 14፤54፣ 66–71
ከዚያም ዶሮው ጮኸ፣ እናም ጴጥሮስ ኢየሱስ ያለውን አስታወሰ፦ ጴጥሮስ ለሶስት ጊዜ ይክደዋል። ጴጥሮስ እያለቀሰ ሄደ።
ማርቆስ 14፥72
የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን ወደ የሮማው ገዥ ጲላጦስ ወሰዱት። ብዙ ሰዎችም አብረው መጡ። መሪዎቹ ጲላጦስ ኢየሱስን እንዲገድለው ፈልገው ነበር። እነርሱም ኢየሱስ ራሱን የአይሁዶች ንጉስ ብሎ እንደጠራ ለጲላጦስ ነገሩት።
ማርቆስ 15፥1–3፤ ሉቃስ 23፥2፤ ዮሀንስ 18፥28–31
ጲላጦስ ኢየሱስን የአይሁዶች ንጉስ እንደሆነ ጠየቀው። ኢየሱስም እንዲህ አለ፣ “መንግሥቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም።” ወደ ምድር የመጣው ህዝብን እውነት ለማስተማር እንደሆነ ገለጸ።
ዮሀንስ 18፥33–37
ጲላጦስ ኢየሱስ ምንም ጥፋት እንደሰራ አላምንም አለ። ነገር ግን ብዙ ሰዎች “ስቀለው” በማለት ጮሁ። ጲላጦስ እነርሱ የፈለጉትን ለማድረግ ወሰነ እና ኢየሱስን አስገደለ።
ማርቆስ 15፥12–14፤ ሉቃስ 23፥14–24