በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
የመጨረሻው እራት—ኢየሱስ ቅዱስ ቁርባንን አስተዋወቀ


ማቴዎስ 26ሉቃስ 22ዮሀንስ 13–14

የመጨረሻው እራት

ኢየሱስ ቅዱስ ቁርባንን አስተዋወቀ

ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ በኢየሩሳሌም ውስጥ።

ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ የአይሁድ ፋሲካን ለማክበር ኢየሩሳሌም ውስጥ ነበሩ። የአይሁድ ህዝብ ፋሲካን በየአመቱ ያከብሩ ነበር። ይህም ከብዙ አመታት በፊት ቤተሰቦቻቸው በግብጽ ውስጥ ባሪያዎች እንደነበሩ እና እግዚአብሔር እንዲያመልጡ እንደረዳቸው ለማስታወስ ይረዳቸው ነበር።

ዘፀአት 12፤27

ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ በጠረጴዛ ዙሪያ ተሰብስበው።

በኢየሩሳሌም ውስጥ እያሉ፣ ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ አብረው ልዩ ግብዣ አደረጉ። ኢየሱስ ይህን ግብዣ ከእነርሱ ጋር ለመካፈል በጉጉት ይጠብቅ ነበር።

ሉቃስ 22፥7–15

ኢየሱስ ከሐዋሪያቱ መካከል የአንዱን እግሮች ሲያጥብ።

መብላት ከጨረሱ በኋላ፣ ኢየሱስ በመታጠቢያው ውስጥ ውኃ ጨመረ። የሐዋሪያቱን እግሮች ማጠብ ጀመረ።

ዮሀንስ 13፥4–5

ጴጥሮስ ለምን እግራቸውን እንደሚያጥብ ኢየሱስን ጠየቀው።

የጴጥሮስ ተራ ሲደርስም፣ ኢየሱስ ይህን ለምን እንደሚያደርግ ጠየቀው። እግርን ማጠብ ሰራተኞች ብቻ የሚያደርጉት ነገር ነበር።

ዮሀንስ 13፥6

ኢየሱስ ሐዋሪያቱን እርስ በራስ ስለመዋደድ አስተማራቸው።

ኢየሱስ እግራቸውን የሚያጥበው ለእነርሱ ምሳሌ ለማሳየት እንደሆነ ነገራቸው። እነርሱን እንደወደዳቸው እርስ በርስ እንዲያገለግሉ እና እንዲዋደዱ ፈልጎ ነበር። ይህን ካደረጉ፣ ሰዎች የእርሱ ደቀ መዛሙርት እንደሆኑ ያውቃሉ።

ዮሀንስ ወንል 13፥14–16፣ 34–35

ጴጥሮስ ከኢየሱስ ጋር ሲነጋገር።

ኢየሱስ በቅርብ እንደሚሞት ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው። ጴጥሮስ ለኢየሱስ ለመሞት ፈቃደኛ ነኝ አለ።

ዮሀንስ 13፥36–38

ኢየሱስ ለጴጥሮስ ሲመልስለት።

ነገር ግን ኢየሱስ አስቸጋሪ ጊዜያት እንደሚመጡ ያውቅ ነበር። እርሱም ጴጥሮስ በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ዶሮ ከመጮሁ በፊት ኢየሱስን አላውቅም እንደሚል ለጴጥሮስ ነገረው።

ዮሀንስ 13፥38

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ስለመንፈስ ቅዱስ ሲያስተምር።

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ እንደሚጨነቁ እና እንደሚፈሩ አውቆ ነበር። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክላቸው ቃል ገባላቸው። መንፈስ ቅዱስ ያጽናናቸዋል፣ ያስተምራቸዋል፣ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እንዳስተማራቸው ለማስታወስ ይረዳቸዋል። እንዳይጨነቁ ወይም እንዳይፈሩ ነገራቸው። እንዲህም አለ፣ “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።”

ዮሀንስ 14፥1፣ 15–16፣ 26–27

ኢየሱስ ለቅዱስ ቁርባን ዳቦን ሲቆርስ።

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ሁልጊዜም እንዲያስታውሱት የሚረዳ በጣም ልዩ ነገር አደረገ። ቅዱስ ቁርባንን ሰጣቸው። መጀመሪያ፣ ዳቦውን ባረከ፣ ቆራረጠው፣ እናም ለሐዋሪያቱ ሰጠ። ኢየሱስም ዳቦውን በሚበሉበት ጊዜ ስለ አካሉ እንዲያስቡ ነገራቸው። ለእነርሱ እንደሚሞት እንዲያስታውሱም ጠየቃቸው።

ማቴዎስ 26፥26ሉቃስ 22፥19

ኢየሱስ ወይኑን ለቅዱስ ቁርባን ሲባርከው።

ኢየሱስ ወይኑን በጽዋ ውስጥ ቀዳው። ወይኑን ባረከው እና ሐዋሪያቱ እንዲጠጡት ነገራቸው። ኢየሱስም ወይኑን በሚጠጡበት ጊዜ ስለ ደሙ እንዲያስቡ ነገራቸው። እኛ ንስሀ ለመግባት እና ይቅርታ ለመጠየቅ እንችል ዘንድ እርሱ ለሁሉም ሰዎች ህመም እና ኃጢያቶች እንደሚሰቃይ፣ እንደሚደማ እና እንደሚሞት እንዲያስታውሱ ጠየቃቸው።

ማቴዎስ 26፥27–28ሉቃስ 22፥20

ኢየሱስ ሐዋሪያቱ ትእዛዛቱን እንዲያከብሩ ሲያስተምር።

ከዚያም ኢየሱስ እርሱ እንደ ወይን ግንድ፣ ደቀ መዛሙርቱ ደግሞ እንደ ቅርንጫፎች እንደሆኑ አስረዳ። ቅርንጫፉ ከወይን ግንድ ጋር ተገናኝቶ ከቆየ፣ ፍሬ ያፈራል። ቅርንጫፉ ከወይን ግንድ ጋር ተገናኝቶ ካልቆየ፣ ይሞታል እናም ፍሬ አያፈራም። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ እርስ በርስ በመዋደድ እና ትእዛዛቱን በመጠበቅ ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር ቅርብ ሆነው እንዲቆዩ ፈልጓል።

ዮሀንስ 15፥4–12

ኢየሱስ እና ሐዋሪያቱ ወደ ጌቴሴማኒ ሲራመዱ።

እነዚህን ነገሮች ካስተማረ በኋላ፣ ኢየሱስ እና ሐዋሪያቱ መዝሙር ዘመሩ። ጌቴሴማኒ ወደሚባል የአትክልት ስፍራም ሄዱ።

ማቴዎስ 26፥30