ሉቃስ 2፥39–52
ታዳጊው ኢየሱስ
መማር እና ማደግ
ኢየሱስ በናዝሬት ከተማ ከማርያም እና ከዮሴፍ ጋር አደገ። በጊዜ ሂደት፣ ስለሰማይ አባት በይበልጥ እየተማረ ሄደ። የሰማይ አባት እንዲሰራ የፈለገውን ስራ ለመስራት ተዘጋጀ።
ሉቃስ 2፥39–40፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥12–14
ኢየሱስ የ12 አመት እድሜ ሲሆነው፣ ፋሲካን ለማክበር ከቤተሰቡ እና ከጓደኞቹ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ። ለአያሌ ቀናትም በዚያ ቆዩ።
ሉቃስ 2፧41–43
ወደ ቤታቸው ሲሄዱ ዮሴፍ እና ማርያም ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር እናልነበረ አስተዋሉ። እርሱን ለመፈለግ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ሄዱ። በጣምም ተጨነቁ።
ሉቃስ 2፥44–46
ሶስት ቀናት ያህል ከፈለጉት በኋላ፣ ማርያም እና ዮሴፍ በመጨረሻ ኢየሱስን አገኙት። ስለ ቅዱሳት መጽህፍት ከአንዳንድ መምህራን ጋር እየተነጋገረ ነበር። መምህራኑ ጥያቄዎችን እየጠየቁት ነበር። ኢየሱስ ምን ያህል ያውቅ እና ይረዳ እንደነበር በማወቃቸው ተገረሙ።
ሉቃስ 2፥46–47፤ በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ 46c) ተመልከቱ።
ሊያገኙት ባለመቻላቸው ምን ያህል ተጨንቀው እንደነበር ማርያም ለኢየሱስ ነገረችው። ኢየሱስ የሰማዩ አባቱን ስራ እየሰራ እንደሆነ ተናገረ። ኢየሱስ ከቤተሰቡ ጋር ወደ ናዝሬት ተመለሰ። ማርያምን እና ዮሴፍን ታዟቸዋል።
ሉቃስ 2፥48–52
ኢየሱስ መማሩን ቀጠለ። እርሱም እያደገ ሄደ፤ ሰውነቱም ጠነከረ።። የሰማይ አባት ወደደው እናም ለተልእኮው እንዲዘጋጅ ረዳው። ኢየሱስ በዙሪያው ያሉትን ሰዎች ወደደ፣ እነርሱም ወደደት።
ሉቃስ 2፥52