1 ቆሮንቶስ 6፥16–20
ጳውሎስ ሰውነታችንን ከቤተመቅደስ ጋር ያነጻጽራል
ከእግዚአብሔር የመጡ የተቀደሱ ስጦታዎች
ቆሮንቶስ በባህር አጠገብ የነበረች ትልቅ ከተማ ነበረች። ከተማዋ እግዚአብሔርን የማያመልኩ ብዙ ሰዎች የነበሩባት ነበረች። ጳውሎስ በቆሮንቶስ ለነበሩ ሰዎች ስለኢየሱስ አስተማረ። ብዙ ሰዎች አምነው ተጠመቁ።
የሐዋርያት ስራ 18፥8–11
ጳውሎስ ከሄደ በኋላ፣ የቤተክርስቲያኗ አባላት አንዳንድ ችግሮች እንደነበሩባቸው ሰማ። ብዙ ሰዎች በቆሮንቶስ ሰውነታችንን እንዴት መያዝ እና መጠቀም እንዳለብን በሚመለከት የእግዚአብሔርን ትእዛዛት አያከብሩም ነበር።
1 ቆሮንቶስ 6፥13–18
ጳውሎስ ደብዳቤ ጻፈላቸው። ሰውነታችን እንደ እግዚአብሔር ቤተመቅደስ እንደሆነ ተናገረ። ቤተመቅደስ የእግዚአብሔር ቤት በመሆኑ በአክብሮት እንጠብቀዋለን። ሰውነታችንም እንዲሁ የእግዚአብሔር ስጦታ ስለሆነ በአክብሮት እንይዘዋለን።
1 ቆሮንቶስ 6፥19–20
የሠማይ አባታችን በሰውነታችን ላይ መልካም ነገሮችን ለማድረግ እንድንመርጥ ይፈልጋል። ይህን ባደረግን ጊዜ፣ መንፈስ ቅዱስ ሁል ጊዜ ከእኛ ጋር ሊኖር ይችላል።
1 ቆሮንቶስ 6፥19
ኢየሱስ ክርስቶስ በስቃዩ ለእኛ ዋጋ እንደከፈለ ተናገረ። ስለ ሰውነታችን መልካም ነገሮችን ስንመርጥ እና የእርሱን ትአዛዛት ስንጠብቅ ለኢየሱስ ያለንን ፍቅር እናሳያለን። ሰውነታችንን እንደቤተመቅደስ በመያዝ ለእግዚአብሔር ስለመልካም ስጦታው አመስጋኞች መሆናችንን እናሳያለን።
1 ቆሮንቶስ 6፥20