ማቴዎስ 3
ኢየሱስ ተጠመቀ
ለእግዚአብሔር ታማኝ የመሆኑን ምሳሌ ማሳየት
ሰዎች ለሚመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲዘጋጁ ለመርዳት እግዚአብሔር ዮሀንስን ሀላፊነት ሰጠው። ዮሐንስ ሰዎችን ንስሐ እንዲገቡ እና እንዲጠመቁ አስተማራቸው። ሰዎችም መጥምቁ ዮሐንስ በማለት ጠሩት።
ማቴዎስ 3፥1–12
ዮሐንስ ሃያል መምህር ነበር። አያሌ ሰዎች እርሱን ለመስማት እና ለመጠመቅ መጡ። አንድ ቀን ኢየሱስ ሊጠመቅ መጣ።
ማቴዎስ 3፥5፣ 13
ኢየሱስ ዘወትር ለእግዚአብሔር ታዛዥ እንደነበር ዮሐንስ ያውቅ ነበር። ንሰሃ መግባት አላስፈለገውም። ዮሐንስ ኢየሱስን ማጥመቅ እንደሚገባው አላመነም። ዮሐንስ ራሱ በኢየሱስ መጠመቅ እንደሚገባ አሰበ።
ማቴዎስ 3፥14
ኢየሱስ እርሱም መጠመቅ እንደሚያስፈልገው ተናገረ። እርሱ የአባቱን ትዕዛዛት በሙሉ ለማክበር ፈለገ። ለእኛም ምሳሌን ለመተውም ፈለገ። ዮሀንስ ጠመቀው።
ማቲዮስ 3፥ 13–15፤ 2 ኔፊ 31፥5–7
ኢየሱስ ከውሃው ከወጣ በኋላ፣ መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ በእርግብ አምሳል ወረደ። የሰማይ አባት “የምወደው ልጄ ይህ ነው” በማለት ከሰማይ ተናገረ። የሰማይ አባት በኢየሱስ እጅግ ደስተኛ ነበር።
ማቴዎስ 3፥16–17