በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስ አላዛርን ከሞት አስነሳው—’’እኔ ትንሳኤ እና ህይወት ነኝ’’


ዮሐንስ 11፥1–46

ኢየሱስ አላዛርን ከሞት አስነሳው

’’እኔ ትንሳኤ እና ህይወት ነኝ’’

ማርያም፣ ማርታ እና አልዓዛር።

ማርያም፣ ማርታ፣ እና አልአዛር ቢታንያ በተባለ መንደር ይኖሩ ነበር። በኢየሱስ ክርስቶስ አምነዋል፣ እርሱም ይወዳቸው ነበር። ማርያም እና ማርታ የአልአዛር እህቶች ነበሩ።

ዮሀንስ 11፥1፣ 5

አልዓዛር ታመመ።

አልዓዛር በጣም ታመመ። ኢየሱስ በሌላ ከተማ ነበር። ማርያም እና ማርታ ኢየሱስ ጓደኛው አልዓዛር እንደታመመ እንዲያውቅ መልእክት ላኩበት።

ዮሐንስ 11፥1-3

ኢየሱስ አላዛርን ከሞት እንደሚያስነሳው ተናገረ።

ኢየሱስ ለሁለት ቀናት ያህል ቆየ። ከዚያም ለደቀ መዛሙርቱ ወደ ቢታንያ እንደሚሄዱ ነገራቸው፡፡ ደቀመዛሙርቱም ተጨነቁ ምክንያቱም በቢታንያ አካባቢ ያሉ አንዳንድ ሰዎች ኢየሱስን ሊጎዱት ይፈልጉ ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ አልአዛርን ለመርዳት ፈልጎ ነበር። ኢየሱስም አልአዛር በዚህ ጊዜ እንደሞተ ተናገረ፣ እናም ከሞት ሊያስነሳው ፈለገ።

ዮሐንስ 11፥6-16

ማርታ ኢየሱስን ስታገኘው።

ማርታ ኢየሱስን ከከተማ ውጪ አገኘችው። ኢየሱስ አስቀድሞ መጥቶ ቢሆን ኖሮ አልአዛር አይሞትም ነበር አለች። ኢየሱስ አልአዛር ዳግም መኖር እንደሚችል ቃል ገባ።

ዮሐንስ 11፥17-24

ማርታ ኢየሱስን ስታናግር።

ኢየሱስም፣ “እኔ ትንሳኤ እና ህይወት ነኝ” አለ። እርሱም ማርታን በእርሱ ታምን እንደሆነ ጠየቃት፡፡ እርሷም፣ “አንተ ክርስቶስ መሆንህን እና እግዚአብሔርም ልጅ እንደሆንክ አምናለሁ’’ አለች።

ዮሀንስ 11፥25-27።

ማርታ፣ ማርያም፣ እና ኢየሱስ።

ማርታ ወደ ቤቷ ተመልሳ ሄደች እናም ኢየሱስ እንደመጣ ለማርያም ነገረቻት። ስለወንድሟ እያለቀሰች ማርያም መጥታ በኢየሱስ እግር ላይ ወደቀች። ኢየሱስም አለቀሰ። አልአዛርን፣ ማርያምን እና ማርታን ይወዳቸው ነበር።

ዮሐንስ 11፥28-36

ኢየሱስ አልአዛር ወደተቀበረበት መቃብር ሄደ።

ኢየሱስ፣ ማርታ፣ ማርያም፣ እና ሌሎችም አልአዛር ወደተቀበረበት መቃብር ሄዱ። ታላቅም ድንጋይ መቃብሩን ሸፍኖት ነበር። ኢየሱስም ድንጋዩን እንዲያነሱት ነገራቸው።

ዮሐንስ 11፥38-39

ኢየሱስ ለማርታ በእርሱ እንድታምን ነገራት።

ነገር ግን ማርታ አልአዛር ከሞተ አራት ቀን እንደሆነው ለኢየሱስ ነገረችው። ኢየሱስ ለማርታ ቃል ስለገባላት ነገር አስታወሳት። በእርሱ እንድታምን ጠየቃት።

ዮሐንስ 11፥39-40

ኢየሱስም አልአዛርን እንዲወጣ አዘዘው።

ኢየሱስም ወደ አባቱ ጸለየ። ሁል ጊዜ ስለሚሰማው እግዚአብሔርን አመሰገነ። ኢየሱስ እግዚአብሄር አዳኝ እንዲሆን እንደላከው ህዝቡ እንዲያምኑ ፈለገ። ኢየሱስም “አልዓዛር ሆይ፣ ተነሳ” በማለት ተጣራ።

ዮሐንስ 11፥41-43

አልዓዛርም እየተራመደ ከመቃብሩ ወጣ።

አልዓዛርም እየተራመደ ከመቃብሩ ወጣ። እርሱም በተቀበረበት ጨርቅ እና መከፈኛ ተጠቅልሎ ነበር። ኢየሱስም ለህዝቡ እንዲፈቱት ነገራቸው። በዚያ ከነበሩት ብዙዎችም በዚያ ቀን በእውነት ኢየሱስ አዳኝ፣ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አመኑ።

ዮሐንስ 11፥44–45