በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
የኢየሱስ ሐዋርያት ቤተክርስቲያኑን ይመራሉ—ማስተማር፣ ማጥመቅ፣ መፈወስ እና ሁሉንም ነገር ማካፈል


የሐዋሪያት ስራ 1–4

የኢየሱስ ሐዋርያት ቤተክርስቲያኑን ይመራሉ

ማስተማር፣ ማጥመቅ፣ መፈወስ እና ሁሉንም ነገር ማካፈል

ሐዋርያት ወንጌልን ያስተምራሉ።

ኢየሱስ ወደ ሰማይ አባቱ ከተመለሰ በኋላ፣ ሐዋርያት የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ነበሩ። የአዳኙን ወንጌል አስተምረዋል፣ ሰዎች ወደ እርሱ ቤተክርስቲያን እንዲቀላቀሉ ጋብዘዋል፣ እና በእግዚአብሔር ኃይል ብዙ ተአምራትን አድርገዋል። ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን በመላክ እንደሚረዳቸው ቃል ገብቷል።

የሐዋርያት ስራ1፥8–132፥41–47

ሐዋርያት ማትያስን ሾሙ።

ይሁዳ ስለሞተ አስራ አንድ ሐዋርያት ብቻ ነበሩ። ሐዋርያት እግዚአብሔር ይሁዳን ለመተካት እና የኢየሱስ ክርስቶስ ልዩ ምስክር ለመሆን ማን እንደሚፈልግ ለማወቅ ጸለዩ። እግዚአብሔር ማትያስ የተባለውን ሰው መረጠ። ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ሆነ።

የሐዋርያት ስራ 1፥15–26

ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሞልተዋል።

በልዩ የአይሁድ በዓል ላይ ደቀ መዛሙርቱ በኢየሩሳሌም አብረው ነበሩ። ድንገት ከሰማይ የመጣ ነፋስ ቤቱን የሞላው መሰለ። እነርሱም እንደ እሳት የሚመስል ብርሃን በላያቸው ሲያርፍ አዩ፤ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ነበር። በመንፈስ ቅዱስ ምክንያት በሌሎች ቋንቋዎች መናገር ይችሉ ነበር።

የሐዋርያት ስራ 2፥1–4

ሰዎች ሐዋርያት ሲናገሩ ለመስማት ተሰብስበው ነበር።

በኢየሩሳሌም የነበሩት ሕዝብ ይህን በሰሙ ጊዜ ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ። ምንም እንኳን በሕዝቡ መካከል ያሉት ሰዎች ከብዙ አገሮች የመጡ እና የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ ቢሆኑም፣ እያንዳንዱም ሐዋርያት በእነርሱ ቋንቋ የሚናገሩትን ሰምተው ነበር። ሰዎቹ በጣም ተደነቁ!

የሐዋርያት ስራ 2፥5–13

ጴጥሮስ ምስክርነቱን ሰጠ።

ጴጥሮስም ቆሞ ለሕዝቡ ተናገረ። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነገራቸው። ኢየሱስ አዳኝ መሆኑን እና ከሞት መነሳቱን መሰከረ።

የሐዋርያት ስራ 2፥14–36

ህዝቡ ሕይወታቸውን እንዴት መለወጥ እንደሚችሉ ሐዋርያቱን ጠየቁ።

ሕዝቡ ይህን ሲሰሙ መለወጥ እንዳለባቸው ተሰማቸው። ሐዋርያትንም ምን ማድረግ እንዳለባቸው ጠየቋቸው።

የሐዋርያት ስራ 2፥37

ሰዎች እየተጠመቁ።

ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፡— “ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፥ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።” በዚያን ቀን ወደ 3,000 የሚጠጉ ሰዎች ተጠምቀው ወደ ቤተክርስቲያኗ ተቀላቀሉ።

የሐዋርያት ስራ 2፥38–43

መራመድ የማይችል ሰው በቤተመቅደሱ ፊት ለፊት።

በኋላም ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ቤተመቅደስ ሄዱ። መራመድ የማይችል ሰው አዩ። በየቀኑ እዚያ ተቀምጦ ሰዎችን ገንዘብ ይለምን ነበር።

የሐዋርያት ስራ 3፥1–2

ጴጥሮስና ዮሐንስ ሰውየውን አነጋገሩት።

ሰውየውም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ገንዘብ ጠየቀ። እነርሱም ቆም ብለው ተመለከቱት። ጴጥሮስም፣ “ወደ እኛ ተመልከት” አለው።

የሐዋርያት ስራ 3፥3–4

ሰውየው በእግዚአብሔር ኃይል ተፈወሰ እና መቆም ቻለ።

ጴጥሮስም ብርም ሆነ ወርቅ እንደሌላቸው ተናገረ። ግን የተሻለ ነገር ነበራቸው። “በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ” አለው። ጴጥሮስም እንዲቆም ረዳው። በሕይወቱ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰውየው መራመድ ቻለ! በጣም ስለተደሰተ እየዘለለም ከጴጥሮስና ከዮሐንስ ጋር ወደ ቤተመቅደስ ገባ።

የሐዋርያት ስራ 3፥6–8

ጴጥሮስ ሰዎች ንስሐ እንዲገቡ እና በኢየሱስ እንዲያምኑ ነገራቸው።

ሰዎቹ በጣም ተደነቁ። ጴጥሮስም ሰውየውን የፈወሰው በእርሱ ኃይልና በዮሐንስ ኃይል እንዳልሆነ ነገራቸው። እርሱ የተፈወሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይልና በእርሱ በማመን ነው። ጴጥሮስም ንስሐ እንዲገቡ እና በኢየሱስ እንዲያምኑ ነገራቸው።

የሐዋርያት ስራ 3፥9–26

አንዳንድ መሪዎች ጴጥሮስንና ዮሐንስን ስለ ኢየሱስ ማስተማር እንደማይችሉ ነገሯቸው።

ከአይሁድ መሪዎች መካከል አንዳንዶቹ ጴጥሮስና ዮሐንስ የሚያስተምሩትን ነገር አልወደዱትም። ስለ ኢየሱስ ማንም ሊያስተምር አልተፈቀደለትም አሉ።

የሐዋርያት ስራ 4፥1–18

ጴጥሮስና ዮሐንስ እግዚአብሔር ሰዎች ስለ ኢየሱስ እንዲያውቁ እንደሚፈልግ ለመሪዎቹ ነገሯቸው።

ጴጥሮስና ዮሐንስ እግዚአብሔርን እንታዘዛለን እንዲሁም እግዚአብሔርም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያውቁትን ለሰዎች እንዲነግሯቸው ይፈልጋል አሉ።

የሐዋሪያት ስራ 4፥19–20

ጴጥሮስ አንዲት ሴት ሲያጠምቅ ሰዎች ተሰበሰቡ።

ሐዋርያት የአዳኙን ወንጌል በታላቅ ኃይል በማስተማር ቀጠሉ። ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያኗ ተቀላቀሉ። በመንፈስ ተሞልተውም ነበር። እርስ በርሳቸው ይዋደዱ እና ሁሉንም ነገር ይካፈሉ ነበር። ያላቸውን ሸጡ እናም ለድሆች ይሰጡ ዘንድ ገንዘቡን ለሐዋርያት ሰጡ።

የሐዋርያት ስራ 4፥31–37