በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ለደህንነት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ መደገፍ—በጸጋው መዳን


ሮሜ 3፥21–285፥1–116፥3–6

ለደህንነት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ መደገፍ

በጸጋው መዳን

ሰዎች እየተጠመቁ።

ከተለያዩ አከባቢዎች ሰዎች የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እየተቀላቀሉ ነበሩ። የቤተክርስቲያኗ አባላት ቅዱሳን ተብለው ይጠሩ ነበር።

ሮሜ 1፥7

ሁለት ሰዎች ስለሙሴ ህግ እያወሩ።

አንዳንዶቹ ቅዱሳን አሁንም የሙሴን ህግ ይከተሉ የነበሩ አይሁዳውያን ነበሩ። ሌሎቹ ግን አልነበሩም። የሙሴን ህግ ያስፈልጋቸው ይሆን አይሁን በሚል በመካከላቸው አለመስማማት ነበር።

ሮሜ 2፥14–15፤ 23–29

ጳውሎስ ደብዳቤ እየጻፈ።

ጳውሎስ ቅዱሳን ይህ ጥያቄ እንደሚኖራቸው ያውቅ ነበር። እርሱም በሮሜ ለነበሩት ቅዱሳን ደብዳቤ ይጽፍላቸው ነበር። የሙሴን ህግ ለመከተል በመሞከር ብቻ ማንም ሰው ሊድን እንደማይችል ነገራቸው። ሁላችንም ሃጢያት ሰርተናል በማለት አብራራ። ለመዳን፣ እያንዳንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ሊኖረው እና እርሱንም ሊከተል ይገባዋል።

ሮሜ 3፥20–23

ሁለቱ ሰዎች የጳውሎስን ደብዳቤ እያነበቡ።

ጳውሎስም እግዚአብሔር ሃጢያታችንን በራሱ ያኖር ዘንድ ልጁን ኢየሱስን እንደላከ አስተማረ። በኢየሱስ ክርስቶስ መስዋአትነት ምክንያት፣ ንስሀ መግባት እና ለኃጢያታች ምህረትን ማግኘት እንችላለን።

ሮሜ 3፥24–31

ሁለት ሰዎች በአንድነት ቅዱስ ቁርባንን እየወሰዱ።

ጳውሎስ ኢየሱስ ክርስቶስ ይቅርታን እና መልካምን ማድረግ እንችል ዘንድ ጥንካሬን እንደሚሰጠን አስተማረ። ይህ የተወደደ ስጦታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ይባላል፣ እንዲሁም በተስፋ እና በሃሴት ይሞላናል። ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳደረገው ስንጠመቅ፣ እንደ ኢየሱስ ተከታይ በመሆን አዲስ ህይወት እንደምንጀምር ጳውሎስ አስተምሯል።

ሮሜ 5፥1–116፥3–6