በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
የደጉ ሳምራዊ ምሳሌ—ራሳችንን እንደምንወድ ባልንጀሮቻችንን መውደድ


ሉቃስ 10፥25–37

የየደጉ ሳምራዊ ምሳሌ

ራሳችንን እንደምንወድ ባልንጀሮቻችንን መውደድ

አንድ ሰው ኢየሱስን አንድ ጥያቄ ጠየቀው።

አንድ የህግ ሰው ኢየሱስን የዘላለም ሕይወትን ለመውረስ ምን ማድረግ እንዳለበት ጠየቀው። ኢየሱስም በቅዱሳት መጻህፍት ምን እንደተጻፈ ጠየቀው። ህግ አዋቂውም ቅዱሳት መጻህፍት እግዚአብሔርን እና ባልንጀራን ውደድ የሚል መሆኑን መለሰለት። ኢየሱስም ትክክል እንደሆነ ተናገረ። ህግ አዋቂውም እንዲህ ሲል ጠየቀ፣ ‘’ባልንጀራዬ ማን ነው?’’ ኢየሱስም አንድን ታሪክ ወይም ምሳሌ በመናገር መለሰለት።

ሉቃስ 10፥25-29

አንድ አይሁዳዊ በወንበዴዎች ቆሰለ።

በምሳሌው ውስጥ፣ አንድ አይሁዳዊ የሆነ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ እያሪኮ በሚወስድ መንገድ እየተጓዘ ነበር። በድንገትም ወንበዴዎች መጡ። ልብሱን ሰረቁት፣ እጅግም ጎዱት፣ እና በዚያ ትተውት ሄዱ።

ሉቃስ 10፥30

ካህኑ የቆሰለውን ሰው እንዳላየ አልፎት ሄደ።

ወዲያውኑም፣ አንድ ካህን በመንገድ እያለፈ ነበር። ካህን በቤተ መቅደስ የሚሰራ ሰው ነበር። አንድን ሰው በመንገዱ አየ ነገር ግን በሌላ አቅጣጫ ተሻግሮ ሄደ።

ሉቃስ 10፥31

ሌዋዊውም የቆሰለውን ሰው እንዳላየ አልፎት ሄደ።

ቀጥሎም ሌላ በመቅደስ ያገለግል የነበረ ሌዋዊ የሚባል አንድ ሰው መጣ። እርሱም የተጎዳውን ሰው አየ፣ ነገር ግን የመንገዱን ሌላ አቅጣጫ ይዞ እንዲሁ አለፈ።

ሉቃስ 10፥32

ሳምራዊውም አይሁዳዊውን ሰው ተመለከተ።

ከዚያም ሳምራዊው ያልፍ ነበር። በመንገዱ ላይ ያለው ሰው እጅግ እንደተጎዳ አየ። የሰማሪያ ሰዎች እና የአይሁድ ሰዎች በአብዛኛው አይስማሙም ነበር። ነገር ግን ይህ ሳምራዊ ሰውየውን ሊረዳ ወደደ።

ሉቃስ 10፥33

ሳምራዊው አይሁዳዊውን ሰው ተንከባከበው።

ሳምራዊው ሰውየውን ዘይት በመቀባት እና በቁስሉም ላይ ወይንን በማድረግ ተንከባከበው። ሰውየውንም በአህያው ላይ አደረገው።

ሉቃስ 10፥34

ሳምራዊውም አይሁዳዊውን ሰው ወደ እንግዶች ማረፊያ ወሰደው።

ከዚያም ሳምራዊው ሰውየውን ወደሚያርፍበት እና ጥበቃ ወደሚደረግለት ወደ እንግዶች ማረፊያ ወሰደው። በነገውም ሳምራዊው ከመሄዱ አስቀድሞ፣ ለጠባቂው ገንዘብ ሰጥቶ እንዲህ አለው፣ ‘’ተንከባከበው።’’ ሳምራዊው ከሌላ ገንዘብ ጋር በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚመለስ ነገረው።

ሉቃስ 10፧34–35

ኢየሱስም ለህግ አዋቂው ልክ እንደሳምራዊው እንዲሆን ነገረው።

በታሪኩ መጨረሻ ላይ፣ ኢየሱስ ህግ አዋቂውን አንድ ጥያቄ ጠየቀው። የተጎዳው ሰው ባልንጀራ ማን ነበር? ካህኑ፣ ሌዋዊው፣ ወይስ ሳምራዊው? የህግ አዋቂውም ለሰውየው ፍቅርን ያሳየው እርሱ--ሳምራዊው ነው ብሎ መለሰለት። ኢየሱስም ለህግ አዋቂው ልክ እንደሳምራዊው እንዲሆን ነገረው።

ሉቃስ 10፥36–37