በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ዘኬዎስ የቀራጮች አለቃ—ኢየሱስን ለማየት ዛፍ ላይ መውጣት


ሉቃስ 19፥1–10

ዘኬዎስ የቀራጮች አለቃ

ኢየሱስን ለማየት ዛፍ ላይ መውጣት

ዘኬዎስ የቀራጮች አለቃ ነበር።

ኢየሱስ የኢያሪኮ ከተማን ጎበኘ። ዘኬዎስ የሚባል ሰው እዚያ ይኖር ነበር። ዘኬዎስ ሀብታም የቀራጮች አለቃ ነበር። ብዙ ሰዎች ቀራጮችን አይወዱም ነበር። ቀራጮች ከህዝቡ ብዙ ገንዘብ ይወስዳሉ ብለው ያስቡ ነበር።

ሉቃስ 19፥1–2

ዘኬዎስ በህዝቡ መካከል ኢየሱስን ለማየት ሞከረ።

ኢየሱስ በከተማው ውስጥ እንደሚገኝ ሰማ። ስለ እርሱ የበለጠ ለማወቅ ፈለገ። ኢየሱስን ለማየት ፈለገ፣ ነገር ግን ብዙ ሰዎች ስለነበሩ ዘኬዎስ ከእነርሱ አልፎ ለማየት በጣም አጭር ስለነበር ለማየት አልቻለም። ኢየሱስን ማየት የሚችለው እንዴት ነበር?

ሉቃስ 19፥3–4

ዘኬዎስ ኢየሱስን ለማየት ይችል ዘንድ ዛፍ ላይ ወጣ።

ዘኬዎስ ኢየሱስን ያየው ዘንድ ወደ ፊት ሮጦ በአንድ ዛፍ ላይ ወጣ። ኢየሱስ በዚያ ሲያልፍ ቀና አለና ዘኬዎስን አየው። ኢየሱስም ሰሙን ጠራው እና “ውረድ” አለው። ኢየሱስ እርሱን በቤቱ ውስጥ ሊጎበኘው ፈልጎ ነበር። ዘኬዎስ ከዛፉ በፍጥነት ወረደ። ኢየሱስ ወደእርሱ ቤት መምጣቱ አስደስቶት ነበር።

ሉቃስ 19፥4–6

ኢየሱስ የዘኬዎስን ቤት ጎበኘ።

የኢያሪኮ ህዝብ ኢየሱስ ለምን ወደ ዘኬዎስ ቤት እንደሄደ ግራ ተጋብተው ነበር። ዘኬዎስ ቀራጭ ስለነበር ኃጢያተኛ ነው ብለው ያስቡ ነበር።

ሉቃስ 19፥7

ኢየሱስ ከዘኬዎስ እና ቤተሰቡ ጋር ተነጋገረ።

ዘኬዎስ ኢየሱስን “ካለኝ ሁሉ እኵሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ” ብሎ ነገረው። ከሰው ብዙ ገንዘብ ከወሰድኩኝም፣ ከዚያ በላይም መልሼ እሰጣለሁም አለ። ኢየሱስ ዘኬዎስን “ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል” ብሎ ነገረው። ኢየሱስ የጠፉትን ሰዎች ለማግኘት እና ለማዳን መጥቻለሁ አለ።

ሉቃስ 19፥6፣ 8–10