በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል ምንም የለም—ህይወት በሚከብድበት ጊዜ የሚረዳ የተሰጠ ተስፋ


ሮሜ 8፥18–39

ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል ምንም የለም

ህይወት በሚከብድበት ጊዜ የሚረዳ የተሰጠ ተስፋ

ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች ደብዳቤ እየጻፈ። በአንድ የቤተክርስቲያኗ አባል ላይ ሰዎች ክፉን ሲያደርጉበት።

ሮሜ አያሌ ህዝብ ያለባት በጣም ትልቅ ከተማ ነበረች። አንዳንዶቹ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ ነበሩ፣ አብዛኞቹ ግን አልነበሩም። በሮሜ ያልይ ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ሲያስተምር ከነበረው እጅግ የተለየ ነገር ያምኑ ነበር። አንዳንድ ጊዜ በሮሜ የነበሩ ሰዎች የቤተክርስቲያኗ አባላት ላይ ክፉን ያደርጉባቸው ነበር።

የቤተክርስቲያኗ አባል ሲጸልይ እና መነሳሳትን ሲቀበል።

ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ ለነበሩት ቅዱሳን ደብዳቤ ጻፈላቸው። ምንም እንኳ ህይወት አንዳንድ ጊዜ ከባድ ቢሆንም እግዚአብሔር ለቅዱሳን የሚሰጣቸው ታላቅ በረከቶች እንዳሉት እንዲያውቁ ይፈልግ ነበር ። እግዚአብሔርን የምንወድ ከሆነ፣ እርሱም በህይወታችን ከባድ የሆኑትን ነገሮች ወደ መልካም ነገሮች እንዲቀየሩ ይረዳናል።

ሮሜ 8፥18፣ 28

ለእርሷ መልካም ያልነበረን ግለሰብ እየረዳች ያለች የቤተክርስቲያን አባል።

ከኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል ምንም እንደሌለ ጳውሎስ ጻፈ። ምንም እንኳ ተግዳሮቶቻችን ከባድ ቢሆኑም፣ እርሱ እንድናልፋቸው ሊረዳን ይችላል።

ሮሜ 8፥31፣35–39