በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስ ሕፃናትን ባረከ—’’መንግስተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ናትና’’


ማርቆስ 10፧13–16

ኢየሱስ ሕፃናትን ባረከ

’’መንግስተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ናትና’’

ሰዎች ሕፃናትን እንዲባርክላቸው ኢየሱስን ጠየቁት።

ኢየሱስ እያስተማረ እያለ፣ አንዳንድ ሰዎች ታዳጊ ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስ ሕፃናቶቹን እንዲባርክላቸው ፈለጉ። የእርሱም ደቀመዛሙርት ሊያስቆሟቸው ሞከሩ።

ማቴዎስ 19፥13ማርቆስ 10፥13

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ እንደ ሕፃናት እንዲሆኑ አስተማራቸው።

ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ሕፃናትን ወደ እርሱ እንዲያመጧቸው ነገራቸው። ሕፃናት በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ያሉ መሆናቸውን ተናገረ። እርሱም ማንም ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ዳግም ለመኖር የሚሻ ቢሆን፣ እንደ ሕፃናት መሆን እንዳለበት ገለጸላቸው።

ማቴዎስ 19፥14ማርቆስ 10፥14-15

ኢየሱስ ሕፃናትን ባረከ።

ከዚያም ኢየሱስ ሕፃናትን ወደ እጆቹ አስጠግቶ ባረካቸው።

ማቴዎስ 19፥15ማርቆስ 10፥16