በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
መጥታችሁ እዩ—ጓደኛ ኢየሱስን እንዲከተል መጋበዝ


ዮሐንስ 3፥43–51

መጥታችሁ እዩ

ጓደኛ ኢየሱስን እንዲከተል መጋበዝ

ኢየሱስ ሰዎችን እያስተማረ እያለ ፊልጶስ ሲያደምጠው።

ፊልጶስ የተባለ ሰው ከኢየሱስ ተከታዮች አንዱ ነበር። እርሱም ኢየሱስ አዳኝ እንደነበር አውቋል። ፊልጶስ ጓደኛው ናትናኤል እንዲሁ ኢየሱስን እንዲያውቅ ፈልጓል።

ዮሐንስ 1፥43–45

ፊልጶስ ከጓደኛው ናትናኤል ጋር ሲነጋገር።

ናትናኤል ቅዱሳት መጻህፍት እግዚአብሔር አዳኝን ይልካል እንደሚሉ ያውቅ ነበር። ፊልጶስ አዳኙን እንዳገኘ ነገረው–እርሱም ከናዝሬት የመጣው ኢየሱስ ነበር።

ዮሀንስ 1፥45

ፊሊጶስ ናትናኤልን እንዲመጣ እና ኢየሱስን እንዲያየው ሲጋብዘው።

በመጀመሪያ ናትናኤል አላመነውም ነበር። አዳኙ ከናዝሬት ሊመጣ እንደሚችል አላሰበም ነበር። “ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን?” በማለት ጠየቀ። ፊልጶስም፣ “መጥተህ እይ” በማለት መለሰ።

ዮሐንስ 1፥46

ኢየሱስ ለናትናኤል ሰላምታ ሲሰጥ።

ናትናኤል ኢየሱስን ለማግኘት ከፊሊጶስ ጋር ሄደ። ኢየሱስም ሲመጡ ሲያይ፣ ናትናኤል መልካም እና ታማኝ ሰው ነው አለ። ናትናኤልም ተገረመ። ኢየሱስን ከዚህ በፊት በጭራሽ አግኝቶት አያውቅም ነበር። ኢየሱስ እንዴት አወቀው?

ዮሐንስ 1፥47–48

ኢየሱስ ከናትናኤል ጋር ሲነጋገር።

ኢየሱስም ፊሊጶስ እርሱን ከማናገሩ በፊት ከበለስ በታች ተቀምጦ አይቶት እንደነበር ለናትናኤል ነገረው።

ዮሀንስ 1፥48

ናትናኤል ለኢየሱስ ሲሰግድ።

አሁን ናትናኤል ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አወቀ። ኢየሱስም እርሱ ታላላቅ ነገሮችን፣ እንዲሁም መላዕክት ከሰማይ ሲወርዱ እንደማየት የመሰለን ብዙ ነገሮችን፣ በእምነቱ ምክንያት እንደሚያይ ነገረው።

ዮሐንስ 1፥49–51