ያዕቆብ 1–3
ከያዕቆብ የተላከ ደብዳቤ
የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ብቻ ሳይሆን ለመታዘዝ የተሰጠ ግብዣ
ያዕቆብ የማርያም ልጅ እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንድሞች መካከል አንዱ ነበር። ያዕቆብ በኢየሩሳሌም የቤተክርስቲያን መሪ ነበር። በአለም ዙርያ ለነበሩ የእግዚአብሔር ህዝብ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዲኖሩ ለመርዳት ደብዳቤ ጽፏል።
ያዕቆብ 1፥1
“ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው … እግዚአብሔርን ይለምን፣” በማለት ያዕቆብ ጽፏል። ከብዙ አመታት በኋላ፣ ጆሴፍ ስሚዝ የተባለ ወጣት እነዚህን ቃላት አነበበና ስለጥያቄዎቹ ለመጸለይ ወሰነ። በኋላም ጆሴፍ ስሚዝ፣ “የያዕቆብ ምስክርነት ዕውነት ሆኖ አገኘሁት” በማለት ተናገረ። እግዚአብሔር የጆሴፍ ስሚዝን ጸሎት መልሷል፣ የእኛንም እንደዚያው ይመልሳል።
ያዕቆብ 1፥5፣ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥11–17፣ 26
ያዕቆብ ሌሎች ሰዎች የሚናገሩትን በጥንቃቄ መስማት እንዳለብን እና መቆጣት እንደማይገባም ጽፏል። ቁጡ ከሆንን እግዚአብሔርን ልናገለግለው አንችልም።
ያዕቆብ 1፥19–20
የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ብቻ በቂ እንዳልሆነና ልንኖረው እንደሚገባም ያዕቆብ ተናግሯል። “ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ … የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ” በማለት ጽፏል።
ያዕቆብ 1፥22
ያዕቆብ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ መሆን ማለት እንዲሁ እግዚአብሔርን ከማመን በላይ እንደሆነ ገልጿል። እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ ዲያብሎስ እንኳን ያውቃል። የበረዳቸው ወይም የራባቸውን ሰዎች ስናይ፣ አልባሳትን እና ምግብን ልንሰጣቸው ይገባል። መበለቶችን እና ወላጅ አልባ ልጆችን ልንጎበኛቸው ይገባል። ያዕቆብ “ከስራ የተለየ እምነት የሞተ ነው” በማለት ጽፏል።
ያዕቆብ 1፥27፤ 2፥14–20
ያዕቆብ ቅዱሳን ሰዎችን በደግነት ማናገር እንዳለባቸውም ጭምር ማስተማር ፈልጎ ነበር። ለቃላቶቻችን መጠንቀቅ ልክ ፈረስን እንደመምራት እንደሆነ ተናግሯል። በፈረስ አፍ ውስጥ ባለ አነስተኛ የብረት ቁራጭ ትልቅን ፈረስ በልጓም ልንመራ እንችላለን። ቃላቶቻችን ትንሽ ቢሆኑም ሃይለኛ ሊሆኑ ይችላሉ።
ያዕቆብ 3፥2–3
ያዕቆብ ለቃላቶቻችን መጠንቀቅ ልክ መርከብን እንደመምራት እንደሆነ ተናግሯል። መርከብ ትልቅ ቢሆን፣ ነፋስም ሃያል ቢሆን ትንሹን መቅዘፊያ ወይም መልህቅ በመቆጣጠር መርከቡን መምራት እንችላለን። የመርከቡ መሪ እንደ ቃላቶቻችን ነው። የምንለውን መቆጣጠር ከቻልን፣ ትልቅ ልዩነት ልናመጣ እንችላለን።
ያዕቆብ 3፥4–5
ያዕቆብ እንደገለጸው ክፉ ቃላት ታላቅን እሳት እንደሚያስነሳ ነበልባል ናቸው። በፍጥነት በመሰራጨት ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ። ለቃላቶቻችን መጠንቀቅ አስፈላጊ የሆነው በዚህ ምክንያት ነው።
ያዕቆብ 3፥5–6
ወደ ሰማዩ አባታችን ለመጸለይ አንደበታችንን እንደምንጠቀም ያዕቆብ ጽፏል። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ የሰማይ አባት ልጆች ለሆኑት ለመናገር በአንደበታችን አስጸያፊ ቃላትንም እንጠቀማለን። ያዕቆብ ይህ መሆን እንደሌለበት ይናገራል።
ያዕቆብ 3፥9–10
ቅዱሳን መልካም ቃላትን እንዲናገሩ ለማስተማር፣ አንድ የውሃ ምንጭ መራራ እና ጣፋጭ ውሃን ሊያወጣ እንደማይችል አስተማረ። የበለስ ዛፍ ወይራን፣ የወይን ተክል ደግሞ በለስን ሊያፈራ አይችልም። በተመሳሳይ መልኩ፣ በልባችን መልካምነት እና ፍቅር ካለ፣ ቃላቶቻችንም እንዲሁ መልካም እና አፍቃሪ ሊሆኑ ይገባል!
ያዕቆብ 3፥11–18