በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ጣቢታ፣ “በመልካም ነገር የሞላባት” ሴት—በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ወደ ሕይወት ተመለሰች


የሐዋርያት ስራ 9፥36–42

ጣቢታ፣ “መልካም ነገር የሞላባት” ሴት

በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ወደ ሕይወት ተመለሰች

ጣቢታ የሽመና ልብስ ስትሰራ።

ጣቢታ የኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ደቀ መዝሙር ነበረች። እሷም በባሕር ዳር ኢዮጴ በምትባል ከተማ ትኖር ነበር። ድሆችን ማገልገል እና መርዳት ትወድ ነበር።

የሐዋሪያት ሥራ 9፥36

ጣቢታ ልብሱን ለተቸገሩ ሰዎች ትሰጣለች።

ጣቢታ ልብስ ሠርታ ለተቸገሩ ሴቶች ሰጠች። ጣቢታን ይወዷት ነበር።

የሐዋርያት ስራ 9፥39

ጣቢታ ታመመች።

አንድ ቀን ጣቢታ በጠና ታመመች። በጣም ከመታመሟ የተነሳ ሞተች።

የሐዋርያት ስራ 9፥37

ሁለት ሰዎች ጴጥሮስን ለማነጋገር ቸኩለው ሲሄዱ።

በኢዮጴ የነበሩት ሌሎች የቤተክርስቲያን አባላት በጣም አዘኑ። ከኢየሱስ ሐዋርያት አንዱ የሆነው ጴጥሮስ በአቅራቢያው በሚገኝ ከተማ እንደሚገኝ ያውቁ ነበር። ጴጥሮስን ፈጥኖና ወደ እነርሱ እንዲመጣ እንዲጠይቁት ሁለት ሰዎችን ላኩ።

የሐዋርያት ስራ 9፥38

ሰዎችም ጴጥሮስን ወደ ጣቢታ ወሰዱት።

ጴጥሮስም የጣቢታ ሬሳ ወዳለበት መጣ። ጣቢታ የረዳቻቸው አንዳንድ ሴቶች እዚያ ነበሩ። ለጴጥሮስም የሠራችላቸውን ልብስ አሳዩት።

የሐዋርያት ስራ 9፥39

ጴጥሮስ ተንበርክኮ ስለጣቢታ ጸለየ።

ጴጥሮስም ሰዎቹ ሁሉ ከክፍሉ እንዲወጡ ጠየቃቸው። ተንበርክኮ ጸለየ።

የሐዋርያት ስራ 9፥40

ጣቢታ ወደ ሕይወት ተመለሰች።

ጴጥሮስም ከጸለየ በኋላ፣ “ጣቢታ፣ ተነሺ” አላት። ዓይኖን ከፍታ ተቀመጠች ። ጴጥሮስም እንድትቆም ረዳት። እንደገና በህይወት ኖረች! ጴጥሮስም ጓደኞቿ መጥተው እንዲያዩአት ጠራቸው። እነርሱም ተገረሙ! በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ወደ ሕይወት እንደተመለሰች ያውቁ ነበር። ብዙ ሰዎች በእርሱ አመኑ።

የሐዋርያት ስራ 9፥40–42